Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አዲሱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር “እንኳን ደስ ያለዎት” አሉ! ጠቅላይ | YeneTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አዲሱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር “እንኳን ደስ ያለዎት” አሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛን በመተካት የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑትን የዲአር.ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲን በአዲስ አበባ አግኝተዋቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው “እንኳን ደስ ያለዎት፤ መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ” ብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ኢትዮጵያ እንደምትደግፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡ ዲአር ኮንጎ የህብረቱ ሊቀመንር በመሆኗ በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ የደቡብ አፍሪካን የማደራደር ሚና ትቀበላለች፡፡የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ደ/ር ኢ/ር ስለሺ ዲአር.ኮንጎ በግድቡ ድርድር ላይ የሚኖራት ሚና ሚዛናዊ እንደሚሆን ከሰሞኑ መሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa