Get Mystery Box with random crypto!

#መታገስ ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል፡፡ እንዴት አትሉኝም...? ዋናው ነገር | የህይወት ቁልፍ🔐🔑

#መታገስ

ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል፡፡ እንዴት አትሉኝም...?
ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው፡፡

እናንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ፤ አሁን ኩፍ ብሎ፤ አሁን ተጋግር፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበሉ፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው፡፡

ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩላቹ እናንተው ብትሰብሩት የምታገኙት ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው፡፡

የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃላቹ ወዳጆቼ??........መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም! አዎ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም፡፡
ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ፡፡

ሰናይ ቀን

ሼር ማድረግ አይርሱ


#የህይወት_ቁልፍ
Join: @yehiywetqulfoch
Join: @yehiywetqulfoch