Get Mystery Box with random crypto!

ለፈገግታ                              በዐረቡ ምድር  ውስጥ የኖረ  ወንዳ ገረድ | የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

ለፈገግታ
                  
          በዐረቡ ምድር  ውስጥ የኖረ  ወንዳ ገረድ  የውበት ደላላ ነው። ከተለያዩ መንደሮች  ወደርሱ የሚጎርፉ ትዳር ፈላጊዎች ••እባክህን ቆንጂቷን ልጃገረድ ጠቁመን ••እያሉ ይዋደቁለታል።
   በአንድ ወቅት በዚያው አካባቢ የሚኖር መንደርተኛ   መልኳ እማይከፋ  ጸባየ ሠናይ ሴት እንዲጠቁመው ይጠይቀውና  ሳያገኝለት ይቀራል።
           በሌላ ቀን ተመልሶ የመጣውን ይህንኑ ሠውዬ   በጥቂት ቀናት  ሸጋ እንስት እንደሚድረው ቃል ገብቶለት ተለያዪ።•• በዚህኛው ዙር ምን የመሰለች ኮረዳ ካልዳርኩልህ   ይሄን ዠርጋጋ ፂሜን በራስህ እጅ ትላጨዋለህ••    ብሎት ነበር የሸኘው እርግጠኛ እንዲሆንለት።
        ቃል እንደገባው ከአንዲት የዐረብ ሸጊት አገናኝቶት ትዳሩን አሰመረለት።ሴቲቷ አበልሁር ካጋነነላት በላይ  መልከኛ እና ጸባይተኛ ነበረች።
        ነገር ወዲህ ነው....  በጫጉላ ሽርሽራቸው ሠሞን በአንደኛው የሙሽሮቹ  ሌሊት ላይ  የአዲሱ ጎጆ በር ተንኳኳ። ከጣፈጠ ወግ ያደፋረሳቸውን የበር ጩኸት የሰሙት ሙሽሮች ቆጣ ባለ  ድምጽ ••ማነው ደሞ በዚ ሌሊት ሚያንኳኳ ያ አሏህ?...እህ ማነው•• ብለው ካሉበት ሳይነሱ ምላሽ ጠበቁ።
        ከበሩ ኋላ ያለ አንድ ድምጽ  ••እእ ይቅርታ ሰይዲ እኔ  አበል ሁር   ነኝ  የሙሽሪት ደላላ...ይኸው እርስዎም እንዳይቸገሩ  ጺም የሚላጨውን ኻዲም እና ምላጬን ይዤ መጥቻለሁ•• ሲላቸው።
             ሙሽሮቹ  እይታቸውን ተለዋውጠው ሳቃቸውን እየለቀቁት  በባልየው ምላሽ  አበል ሁርን አሰናበቱት።
      يا أبا الحر  وفر الله لحيتك   ،ارجع إلى منزلتك بسلام
ውይ አበል ሁር አንተ ነህ እንዴ!  በል እንግዲህ አሏህ ፂምህን ያብዛልህ፡ያፋፋልህ። ወደ ቤትህ ተመለስ አሏህ በሰላም ይመልስህ።
       ሚስት በተራዋ... ••ውዴ ግን እንደኪራይ ቤት በደላላ ነው እንዴ ያገኘከኝ??••....የሙሽሪት የጥያቄ ናዳዎች ከነኩርፊያ ለምቦጮቻቸው ይቀጥላሉ.......

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA