Get Mystery Box with random crypto!

#ሀያትና_የአይን_ፍቅር #ክፍል_ስምንት አብዱ ኤምሬ 'በእርግጥ ሙሀመድን ስወልድ የ | የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

#ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_ስምንት

አብዱ ኤምሬ


"በእርግጥ ሙሀመድን ስወልድ የመጀመሪየሰ ልጄ ስለሆነ ብዙ ፈተና አሳልፌለሁ ቀጥሎ ቡሀላ ነቢል ኑራ አህመድ ሰሚርን ወለድኩኝ ሰብሪና ከተለወደች ቡሀላ በአባታችሁ እና በእኔ ለአራት አመት መሀል ግጭት ተፈጥሮ ነበር ግን ለአላህ ምስጋና ይገባውና አሁን ተፈቷል። እናንተን የመሰለ ልጆችን አፍርተናል አሁን ደግሞ ይህው እኔም ወግ ደርሶኝ ልጄን በወግ ማዕረግ ልድር ነው። በቃ ሂዱ ተኙ ደህና እደሩ" ብላ ንግግሮን አቋመች ከሰብሪና ውጪ ሁላችንም ተመስጠን እየሰማን ነበር ሰብሪና በተቀመጠችበት እንቅልፍ ወስዷታል ሰአቱን ሳየው በጣም ሄዷል 5:27 ይላል ሁላችንም ተነስተን በደስታ መንፈስ ወደ መኝታችን ሄደን ተኛን...

ጠዋት ስነሳ በጣም ረፍዷ ነበርና ወደ ት/ቤት አልሄድኩም በእርግጥ አውቄ ነበር የተኛሁ መስዬ ያረፈድኩት ቀኑ ሙሉ የመድረሳ ሰአት እስኪደርስ እና ለሀዩ የልቤን እስክናገር ቸኩያለሁ የማይደርስ የለምና የመድረሳ ሰአት ሲደርስ ሄድኩ የመውጫ ሰአቱ አልደርስ ብሎኛል ምን አለፋችሁ የቀን ያህል ነው የረዘመብኝ ምንም ትምህርቱን መከታታል አልቻልኩም ነበር... ከመድረሳ ቀደም ብዬ ወጥቼ ሀያትን መጠበቅ ጀመርኩ ግን እስካሁን አልወጣችም በመጨረሻ ኢክራም ስትወጣ አየሆት ኢክራምና ሀዩ አብረው ስለሚወጡ በጣም ደስ አለኝ ግን ሀዩ አብራት አልነበረችም ኢክራምም እንደሌላ ጊዜ ሀዩን ቆማ አልጠበቀችም ምን አልባት ትቆይ ይሆናል ብዬ ብጠብቃትም አልወጣችም ምክንያቱም ሀያት አልመጣችም ነበር። ሁሌ ለመናገር ስወስን እንደዚያ አይነት ነገር የሚያጋጥመኝ ለምን ይሆን ልቤ በጣም ተሰብሮል ነገም ልነግራት አልችልም ምክንያቱም ነገ አርብ ስለሆነ መድረሳ የለም መድረሳ ያለው ቅዳሜ ነው ምንም ቢሆን የመናገር ድፍረቱ አሁንም አለኝ ነገር ግን ባትመጣስ አሁንም ሰኞ ድረስ ልጠብቅ ነው...

አርብም ትምህርት መግባት ስለደበረኝ አልገባሁም ለጁመኣ ስግደት በጠዋት ገላዬን ታጥቤ የሰላት ሰአት ሲደርስ ወደ አንዋር መስጂድ ሄድኩ የዛሬው ኹጥባ (ስብከት) ስለ ረመዳን ፆም ነበር የረመዳን ወር የቀረው ወር ያህል ብቻ ነው ረመዳን ሁሉም ሙስሊሞች መምጣቱን የሚናፍቁት ወር ነው ከሰላት ቡሀላ ወደ ቤት ተመለስኩ.. ዛሬም ምሽቱ እማዬ እና አባዬ አድምቀውታል..

ዛሬ ቅዳሜ ነው ሰርጉ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከማሜ ጋር ልብስ ለመግዛት ወደ ቦሌ አከባቢ ያሉ ልብስ ቤቶች ብንሄድም ዋጋቸው አይቀመስምና መርካቶ ሄደን ለማሜ አሪፍ ሱፍ አግኝተን ገዝተናል ለሚዜዎቹም የሚሆነውንም ተከራይተናል እኔ ሚዜ እንድሆን ቢጠይቀኝም ሰው በተሰበሰበበት ጎልቶ መታየት የማልወደው ነገር ነውና ድፍረቱም ስለሌለኝ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም ከግማሽ ቀን መንከራተት ቡሀላ ወደ ቤት ተመለስን ...

እማ ዛሬ በጣም ደስተኛ ሆናለች "ምን ተገኝቷ ነው ይሄ ሁሉ ደስታ " አልኳት ፈገግ እያልኩ አጎቶችህ ሀሙስ ከገጠር እንመጣለን ብለውኛል ለዛ ነው የተደሰትኩት አለች በነገሩ ደስ ቢለኝም ከገጠር ድረስ ሰው ይጠራል ብዬ አላሰብኩም ነበር በዚህ አይነት ምንም ቢደገስ አይበቃም አልኩ በልቤ አሁንም ግን ሀሳቤ ሀዩ እና ሁዩ ጋር ነው በፍቅሮ መስከሬን እስክነግራት ቸኩያለሁ...

ልነግርሽ ያልኩ ለት መውደዴን አውጥቼ:
በሰው ተገፍቼ:
ብታይ ተርበትብቼ:
ድፍረቴን አጥቼ:
በቁም ሳለው ሞቼ:
ሳፈቅርሽ ፈርቼ:
ልቀርበሽ መጥቼ:
ሄዳለው ሸሽቼ:

ልነግርሽ ያልኩለት ፀሀይ ወጥታ ገባች:
ጎሁም ቀደደ ጨረቃም አለፈች:
በጋውም ነጎደ ለክረምት ለቆ:
ልነግርሽ ያልኩለት ድፍረት ከኔ ርቆ።

ይቀጥላል......

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA