Get Mystery Box with random crypto!

መሳጭ የፍቅር ታሪኮች 😀😀😍😁👌👍

የቴሌግራም ቻናል አርማ yedorya5keldoce48 — መሳጭ የፍቅር ታሪኮች 😀😀😍😁👌👍
የቴሌግራም ቻናል አርማ yedorya5keldoce48 — መሳጭ የፍቅር ታሪኮች 😀😀😍😁👌👍
የሰርጥ አድራሻ: @yedorya5keldoce48
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.70K
የሰርጥ መግለጫ

መሳጭ የፍቅር ታሪኮች በዚህ ቻናልሚፈቀደው ማንበብ በቀልዶቹመሳቅ እናመደሰት ብቻነው😆😆😆😆ቀልዶቹ
ሸንት አስጨራሽቀልዶች
መለያችን ነው
😂😂#365ቀንበሳቅ እናሳልፋ
Creator @Azgoooooo
#Leave ከማለታችሁ በፊት ችግሩንአሳውቁን⛔ @Azgoooooo
For any comment &
cross :- @Azgoooooo
Channel created on :- may - 3

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 22:48:13 ማንችስተር ተሸንፎማ እኔ እራት አልበላም ስል...

Mother ምን አለ ሁሌም በተሸነፈ...
224 viewstêsfãyè, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:49:21 የቻናሉ ስም
የዱርዬ ቀልድች ይሁን ምትሉ
የዱርዬ ፍቅር የምትሉ
313 viewstêsfãyè, 05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:39:10 ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ share አርጉ
285 viewstêsfãyè, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:33:38 ​​​ እሺ ውዶቼ እንደምን ቆያቹልኝ። እነሆ ዛሬ ለናንተ የሚሆን ተወዳጅና አስተማሪ ታሪክ ይዤ መጥቻለው።

......... ም ኞት ..........

ምንጭ :- ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ

ክፍል 1
.
.
.
ምኞት ትባላለች ትውልዷ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን እድገታም
ድሬዳዋን የበረሀዋ ንግስት የሚል ተቀፅላ ስም እንዲሰጣት
ምክንያት በሆነችው እድሜ ጠገብ ዛፎች ከበዙባት ከዚራ መንደር
ውስጥ። ምኛት ማንም አይቶ ሳያደንቅ የማያልፋት ቆንጆ ነች ።
ፈጣሪ ቆንጆ ለመባል የሚያስፈልጋትን መስፈርቶች በሙሉ
ሳያጓድል ያደላት። ሂወት የግዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉንም ስሜቶች
የምናጣጥምበትን ደስታ አልያም ሀዘን እንደየ መልካችን እና
እንደየልካችን ላንዱ አሳንሳ ላንዱ አብዝታ እያፈራረቀች ታድላለች
ሁሌም የሚደሰት ወይ ሁሌ የሚያዝን ሰው በምድር ላይ
አይኖርም። ለሁሉም እኩልና ሳታዳላ የምትሰጠው ነገር ቢኖር
ሞትን ብቻ ነው ።ምናልባት እንደየአማማቱ ሞትንም መጥፎና
ጥሩ ብለን መክፈል ብንችልም ።ምኞት በእናት እና አባታ
ድንገተኞ ሞት የደረሰባት ሀዘን ከህቷ ባል ብርቱ ክፋት ጋር
ተደምሮ ያን ታይቶ የማይጠገብ ውበቷን በእሥደንጋጭና
በማይታመን ሁኔታ በአጭር ግዜ ውስጥ እንደጥዋት ጤዛ
አርግፎቷል። ፌስ ቡክ ላይ ያለው ግን ያ ከአይን ያውጣሽ
በምትባልበት ግዜ የነበረ ፎቶዋ ነዉ።ሚክያስ ከአስር አመት በላይ
የስደት ሂወት ቡሀላ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰ ዲያስፖራ
ነው።ምኛትን ይመጀመሪያ ቀን ፌስ ቡክ ላይ ፕሮፋይል ያረገችውን
ፎቶ እንደተመለከተ ነበር እቺ ልጅ ለኔ መሆን እለበት
የተፈጠረችው ያለው ።ያን ቀን ፎቶዋን ወደ ሞባይሉ በመውሰድ
የላከላትን የፌስቡክ ጋደኝነት ጥያቄ መቀበል አለመቀበላን
ለማረጋገጥ ስገባ ሲወጣ የዋለሁ። ፌስ ቡክ ላይ ያሉት ፎቶዎቿ
በሙሉ ከሁለት አመት በፊት በሀዘን ማእበሉ ሳትመታ የተነሳቻቸው
ነበሩ።
በፉት የነበረው ውበታ ባይኖርም በራሥ መተማመኗ ግን እንዳለ
ነዉ፡ ባጭር ግዜ ውስጥ እንዲህ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የገባው
ውበታ ትንሽ ሰላም ብታገኝ ለመመለስ ግዜ እንደማይወስድበት
ታውቀዋለች።፡ ።የቀየዋለሁ።ትሳካለት። ተዋወቃት።
ሞትኩልሽ ፣በፍቅርሽ እበድኩ ህልሜም እውነቴም አንቺ ብቻ ነሽ

ለምን አትመጭም ብቻ ሆነ የየዕለት ወሬው
ምኛት ድሬ ዳዋ ከታላቅ እህታ ጋር ነበር የምትኖረ
ው:ሚኪ በፌስ ቡክና በስልክ እንጂ በአካል የማያውቃት ን
ከተዋወቁ ቡሀላ ብቻዉን መኖር እንደከበደውና
መጥታ አብረው እንዲኖሩ መወትወት የየለት ስራው የሆነው
በተዋወቁ በወሩ ነበር፡ አጭር በሚባል በስድስት ወር ግዜ ውስጥ
አሳመናት። ልባ ወደ ሸገር ኮበለለች
እንድ ቀን በለሊት ተነስታ ሸንጣዋን አውጥታ ልብሷን መከታተት
ስትጀምር
እህቷ ከንቅልፏ በርግጋ ተነሳችና እንዳትሄድ ተማፀንቻት አንድ
ነገር ተፈጥሮ ብትመለስ እቤት እንደማታስገባት በማስጠንቀቅ
ጭምር አስፈራርታ ልታስቀራት ሞከረች።
ምኛት ግን እህታን ልትሰማት እንኳን ፍቃደኛ አልነበረችም። ካንቺ
ባል የባሰ አያጋጥመኝ እያለች ስትልጎመጎም እህታ አልሰማችም
ምኛትም መስማቷን አልፈለገችውም ትዳራቸውን ላለመበጥበጥ
ኧእምሮዋ እስኪቃወስ ችላ የኖረችውን ይህቷን ባል ገበና ዛሬም
በሆዷ እንደያዘችው ሚስጥሯን ቀብራ በቱን ልቃ
ሻንጣዋን ይዛ ወጣች ።መነሀሪያ እንደደረሰች ከቆይታ ቡሀላ ጉዞ
ወደ አዲስ ተጀመረ።
አሁን ተኝቶ ይሆናል ረፈድ ሲል እደውልለታለሁ
ብላ አሰብች፡ ትንሽ እንደሄድ ስልኳ ጠራ እህታ ነበረች
አላነሳችውም ደጋግሞ ሲጠራ አጠገባ የተቀመጠው ሰውዬ ዞሮ
ሲያያት አነሳችውና
ጉዞ ላይ ነኝ አይሰማኝም ብላ ዘጋችው። እህታ ጨክና መሄዷን
ስታረጋግጥ ማልቀስ ጀመረች በእንባዋ ከጎና እንዲሆንና ክፉ ነገር
እንዳይገጥማት ፈጣሪን ከመማፀን በስተቀር ምርጫ አልነበራትም

ጉዞው ቀጠለ ከቆይታ ቡሀላ በድጋሚ ስልኳ ጠራ ዲያስቦራው
ነበር ተነስተሀል እንዴ እየመጣሁ ነው ግን እንቅልፍ ላይ ትሆናለህ
ብዬ ነው ያልደወልኩት
አለችው የኔ ቆንጆ ማታ እንደምትመጪ ከነገርሽኝ ቡሀላ እንቅልፍ
እሚባል ነገር ባይኔ አልዞረም ቶሎ ካልደረሽልኝ መፈንዳቴ ነው
በፕሌን የመሄድ ፎብያ ያለባት ሴት አፍቅሬ በናፍቆት ልሰቃይ
በፕሌን ቢሆንኮ እሄኔ እቅፌ ውስጥ ነሽ ፡ አላት። ሳቀችና በቃ
ስደርስ እደውልላሀለሁ ብላ ዘጋችዉ። ደርሳ ደወለችለት ስልኩን
ጆሮዋ ላይ ሳታደርሰው አንስቶ ደረስሽ ቆንጆ? አላት።እየገባን ነው፡
አለችው። የአውቶብሱን የጎን ቁጥርና የቱጋ እንደምትወርድ
ጠየቃት፡ አጠገቧ ያለውን ሰውዬ ጠይቃ መድቀል አደባባይ
መሆኑን ነገረችው ያውቶብሱን የጎን ቁጥር ሲጠይቃት ከትኬቱ ላይ

ቀድሞ ነበር የደረሰው በጉጉት መጠበቅ ጀመረ ደረሰች ቆሞ
የሚወርደውን ሰው አንድ በአንድ ይመለከታል እሷ ግን ገና
ሳትወርድ ውስጥ ሆና አየችዉ ወርዳ በፈገግታ ወደ እሱ
ተንደረደረች
እንዳያት ደረቱ አከባቢ የሆነ ነገር ፍርስ ሲል ተሰማው ከአይኗና
ከቁመታ ውጪ ያ በ ፌስ ቡክ ያየው ማራኪ ፊትና ቅርፅ እንደሌለ
ሢረዳ ቢደነግጥም ድንጋጤውን ደብቆ
ሰላምታዉን ሞቅ ለማድረግ ሞከረ፡ ቀጥታ ወደ መኪናው ይዟት
ከገባ ቡሀላ መጀመሪያ ሊወስዳት ወደአሰበው ወደ ቤቱ ሳይሆን
ከጒደኞቹ ጋር አንዳንዴ እንደመደበሪያም እንደመደበቂያም በየተራ
ወደ ሚጠቀሙበት በጋራ ወደ ተከራዩት ኮንደሚንየም ይዟት
በረረ...


✎ ክፍል ሁለት ከ50 like በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like50 ማድረግ አይርሱ።

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
296 viewstêsfãyè, 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:20:12 ምኞት የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ አስተማሪ ታሪክ ሊጀመር ስለሆነ
ይጀመር የምትሉ እስኪ
264 viewstêsfãyè, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:46:42 "ይሻላል ማኩረፍሽ"

ወደድኩሽ በስስት
ህይወት በቃኝ ብዬ
ራሴን እስክስት
.
.
አሰብኩሽ ለትዳር
ፍቅር መሀል ሁነን
ብትይም ዳር ዳር
.
.
ወሰንኩኝ ላገባሽ
አናቴ ላይ ወተሽ
እንድትሆኝ እንዳሻሽ
.
.
ቆይ እንዴት ልውደድሽ?
ዉበቱ ታድሎሽ
ከእግር እስከ ራስሽ
.
.
ቆይ እንዴት ላፍቅርሽ?
ከፍቅር መስፈርቶች
እጅጉን እርቀሽ
.
.
አይኖችሽ ውብ ናቸው
እንዴትስ አድርጌ
በምን ልግለፃቸው
ከውበት በስተቀር
እንከን ሳጣባቸው
.
.
የጥርስሽ ፈገግታ
ከሁሉም ይለያል
ልብን ሀሴት ሞልቶ
መንፈስ ያስጨንቃል
.
.
ከቁንጅና ጣሪያ እላይ ተሰቅለሽ
የውበትሽ ፀዳል ከግዜር ተችሮሽ
ከውበት ባህር ውስጥ
በቁምሽ ተዘፍቀሽ
.
.
አንቺን በቃል ብቻ
እንዴትስ ልግለፅሽ
.
ቆንጆ ብቻ ብዬ
ይሻላል ማኩረፍሽ
ወበትሽን እሚገልፅ
ቃል እስካገኝልሽ

,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,, share◉●••
354 viewstêsfãyè, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:37:25 . ልቤ ብቻ ፅኑ

ድሮ ድሮ ድሮ... ድንጋይ ዳቦ እያለ
ሰማይ እንደ ጣሪያ ሳይርቅ ዝቅ እንዳለ
ዶሮም እንዳሞራ መብረር እየቻለ
ታስታውሺ ነበር? እወድሽ ነበረ

ታዲያ ምን ያደርጋል ሁሉም ተቀየረ
ድንጋይ ዳቦ ትቶ ድንጋይ ሆኖ ቀረ
ሰማይ አፈንግጦ እንደዚህ ከፍ አለ
ዶሮም መብረር ትቶ መራመድ ጀመረ
ልቤ ግን ልብ ነው ያኔ እንደነበረ
በዘመኑ ሙሉ ሲያፈቅርሽ የኖረ፡፡


,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,, share◉●••
334 viewstêsfãyè, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:36:41 ልብ ካለሽ ልብሱን ሳይሆን ልቡን ተመልከቺው
389 viewstêsfãyè, 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:35:09 ሠላም ለኢትዮጵያ ሀገራችን ሠላም ለህዝቦቿ
#No_More_War ጦርነት በቃን !!
383 viewstêsfãyè, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:33:11 ሶፍት ይዘሃል ብዬ ስጠይቀው ይገርምሃል ጉንፋን ካልያዘኝ አልይዝም እያለኝ በዚያ ሎሊፖፕ በመሰሉ ጣቶቹ አፍንጫውን ያማስለዋል
#ሶፍት_ግዛ
383 viewstêsfãyè, 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ