Get Mystery Box with random crypto!

ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ወደ ፊልጵስዩስ 1: 22-30 22 ነገር ግን በስጋ መኖር ለ | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ

ወደ ፊልጵስዩስ 1: 22-30

22 ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም።

23 በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ 24 ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።

25 -26 ይህንንም ተረድቼ፥ በእናንተ ዘንድ እንደ ገና ስለ መሆኔ፥ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ።

27 ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።

28 በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ 29 ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤

30 በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት፥ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና።

አሁን እንደው ጳውሎስ ልኑር ወይስ ልሙት የቱን ልምረጥ እያለ ሲቸገር ይገርማል:: ማንም በዚህ ጥያቄ ሲፈተን አይቼ አላውቅም ልኑር ህይወቴን አቅና የሚል እንጂ እኔንም ጨምሮ ያውም ከአንዱ የድብደባ መድረክ ወደሌላው የሚሄደው ጳውሎስ የቱን መምረጥ እንዳለበት ሲቸገር ይደንቃል:: ልክ እንደው ሁለት የሚያጉዋጉዋ ነገር በፊቱ ያለ ይመስላል:: አንድም እየተደበደቡ መኖር አልያም መሞት እና ወደ ጌታ መሄድ:: እሱ እንዳስቀመጠው ግን ለኔ መሞቱና ወደ እረፍት መግባቱ ይሻላል ደግሞም በጣም እናፍቃለሁና ከጌታዬ ጋር መኖርን ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ብቆይ ደግሞ በእኔ መመካታችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ይበዛ ዘንድ፥ በእምነት ታድጉና ደስ ይላችሁ ዘንድ እንድኖር ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ አውቃለሁ ብሎ መቆየቱን መርጧል::

ከራሱ ይልቅ ለሌላ ለመኖር ወሰነ እኛስ ምን እንወስን ይሆን? እራሳችንን ስናይ ግን አንዳች ጎደለን ብለን ወይም ይህ ነገር አልተሳካም ብለን ወደ ጌታ በሄድን ወይም እርሱ በመጣ እምንል ነን:: ምን አይነት የወንጌል መልእክት እንደያዝን አይገባኝም ጌታ ይርዳን ለክርስቶስ አካል እንኑር ብለን ለመኖር ከየት እንደምንጀምርም ግራ ይገባል:: ወንጌል ግን ለጌታ መኖር ነው::

ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ብሎ ይላል እንዴት ነው እንደሚገባ የምንኖረው?

1. በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ – የያዝነው የወንጌል ስራ እንደ አካል በህብረት የሚሰራ ነውና በመዋደድና በመደጋገፍ ልንሰራ ይገባል:: ዮሐንስ 13:35. እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።

2. በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ – 1ኛ ቆሮንቶስ 12
13፤ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል። እናስታውስ ያው አንዱ መንፈስ በሁላችን አለልዩነት አለ::
እንደዚህ ስንመላለስ የጠላት ፉከራና ቀረርቶ አያስፈራንም ምክንያቱም የመዳን ምልክት እንጂ ለእኛ የጥፋት አይደለም::

ክርስቶስን ስንከተል ከወንጌል የተንሳ መከራ ይመጣል ግን አያጠፋንም እናሸንፋለን::