Get Mystery Box with random crypto!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው ወደ ፊልጵስዩስ 1:21 21፤ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው

ወደ ፊልጵስዩስ 1:21

21፤ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።

ዘራፍ!! እያለ ድፍረት ለማግኘት እራሱን እያነቃቃ አይደለም ጳውሎስ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነው ሲለን ውስጡ የሞላውን እውነት ነው የሚነግረን ያለው:: ያስጨነቀው መሞቱ አይደለም ለኔ መሞት ጥቅም ነው ነው ያለው ብኖር እጠቅማችኃለሁ ስለዚህ ስጋዬ በግርፋትና በመከራ ይለፍ እንጂ ነፍሴን መንካት ማንም አይችልም በሚል ልበ ሙሉነት ነው እየተናገረ ያለው:: ለሌላው አካል ወይም እስር ቤት ላስገቡት ቦታም አልሰጣቸው ከእስርም ያስመልጣል ከሞትም ያስነሳል የኔ ጌታ ሁሉ በእጁ ነው እያለ ነው:: ከዚህ በፊት ደብድበው ሞቷል ብለው ጥለውት አልሄዱም? እርሱ ግን ተነስቶ መስበኩን ቀጠለ አይደል? ጌታውን ጠንቅቆ ያውቃል እኛም እንወቀው:: የሚያኖረን ከክርስቶስ የተቀበልነው ጸጋ እንጂ የሰው ቸርነት ወይም የስጋችን ብርታት አይደለም::


ህይወታችን እራሱ ክርስቶስ ነው በእርሱ ውስጥ ነን ካልን እዚህ እንሁን ወይም በሰማይ ምንድነው ለውጡ? በመጀመርያ ግን በእርሱ ውስጥ ነኝ የሚለው ሀሳብ በውስጣችን ሊዘልቅና አይምሯችን በዚህ እውነት ሊሞላ ይገባዋል:: ሞት እኮ መውጊያውን ተነጥቋል ዛሬ መጣሁ እያለ አያስፈራራንም ከሞትም ጋር ህብረትም ወዳጅነትም የለንም:: ለእኛ ሞት ማለት በር ብቻ ነው ወደ ዘለዓለሙ መዝለቂያ እንዲያውም ሊያስፈራን ሳይሆን ስራችንን ስንጨርስ በል አሰናብተኝና ወደቤት ልምጣ የምንልበት ማለፊያ በር ብቻ ነው:: የመጨረሻ የተባለውን ትንፋሽ በዚች ምድር ላይ ስንወስድ ወድያው የመጀመሪያውን በሰማይ እንጀምርና ጌታንም በክብሩ እናየዋለን:: ግን ዛሬ ነፍስና ስጋችንን የሚያላቅቀው ነገር ሞት አይደል?! ዛሬም ጠላት መጣሁብህ እያለ ባዶ እጁን የቀረበትን የሽንፈት መሳሪያውን እንደድል ሲጠቀምበት ዝም አልነው::

ይብቃ እኛ የክርስቶስ ነን!! ማንም ከቶ አያስፈራራንም ብንኖር ለጌታ ብንሞት ለጌታ!

ሃሌሉያ!!!