Get Mystery Box with random crypto!

በሁሉ ምክንያት ክርስቶስ ይሰበክ ወደ ፊልጵስዩስ 1:12-20 12፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

በሁሉ ምክንያት ክርስቶስ ይሰበክ

ወደ ፊልጵስዩስ 1:12-20

12፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህ የደረሰብኝ በእውነት ወንጌልን ለማስፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

13፤ ስለዚህም እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንዲሆን በንጉሥ ዘበኞች ሁሉና በሌሎች ሁሉ ዘንድ ተገልጦአል፥

14፤ በጌታም ካሉት ወንድሞች የሚበዙት ስለ እስራቴ ታምነው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲነግሩ ያለ ፍርሃት ከፊት ይልቅ ይደፍራሉ።

15፤ አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል፤

16፤ እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥

17፤ እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ::

18፤ ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።

19፤ ወደ ፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤ ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መሰጠት ለመዳኔ እንዲሆንልኝ አውቃለሁና፥

20፤ ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።

ወንድማችን ጳውሎስ ወንጌልን ሲሰብክ የደረሰበት ብዙ ድብደባ ብሎም እስራት ነው:: መታሰሩም ወንጀል ሰርቶ ሳይሆን በእምነቱ እንደሆነ ታውቋል:: ይህም ወሬ አሳሪዎቹም ሳይቀሩ አውቀዋል ምናልባትም ወንጌልን ሰምተዋል:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን በእኔ ላይ የመጣውን መከራ እዩ ሳይሆን እያለ ያለው አይዟችሁ መታሰሬ አያሳዝናችሁ በርቱ ወንጌልን ስበኩ እያለ ነው:: እንዲያውም አንዳንድ ወንድሞች እስራትን ንቀው ከፊት ይልቅ ወንጌልን እየሰሩ ነው ይላል ምክንያቱም እርሱ ስለ እስራቱ ሳይሆን የሚያወራው ስለወንጌል መሰበክ ስለሆነ በወገኖች ላይ ያሳደረው ነገር ወንጌል መሮጥ አለበት የሚልና ብያዝ እንኳን ግፋ ቢል መታሰር ነው እንደእርሱ ሳልያዝ ልስራ የሚል መንፈስ ነው:: ሌሎች ደግሞ በማሾፍ የሞተ ተነሳ ይላል ብለው አንዳንዶችም መከራውን ሊያበዙና ወደፊት ስለዚህ ጌታ ሁለተኛ እንዳይናገር ተስፋ ለማስቆረጥ ስለ ኢየሱስ ይናገራሉ::

በዚህ ሁሉ ግን ይላል ኢየሱስ ብቻ ይሰበክ በዚህ ደስ ብሎኛል ይላል::

በህይወት ይሁን በሞት በስጋዬ ጌታ ይክበር ባይ ነው ምክንያቱም አላፍርም በጸሎታችሁና በመንፈሱ ተረድቼ እቆማለሁ ይህ ተስፋዬ ናፍቆቴም ነውና ብሎ ስለ ዘላለም ህይወቱ እንጂ ከስር ስለመፈታቱ አያወራም ሁልጊዜ ወደጌታ ያሳያል ያበረታል:: እኛም ዛሬ አይናችንን በርሱ ላይ አድርገን ወንጌልን እንስበክና እንኑረው::