2022-02-05 14:27:41
ጊዜ
“እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።”
— መክብብ 9፥11
በህይወት ሳለን በደንብ ልንረዳው የሚገባን ነገር ቢኖር ጊዜ የሚለው ነገር ነው። እግዚአብሔር በጊዜ የማይያዝ እና በዘላለም ውስጥ የሚኖር አምላክ ቢሆንም ነገሮችን በምድር ላይ የሚሰራው ግን በጊዜ ውስጥ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ጊዜ አለው ይላል። በምድር ላይ ሁሉም ነገር ጊዜ አለው። በጊዜ ውስጥ ታናናሾች ታላላቅ ይሆናሉ። በጊዜ ውስጥ ታላላቆች ታናናሽ ይሆናሉ። በጊዜ ውስጥ የወደድነውን እንጠላለን። በጊዜ ውስጥ የጠላነውን እንወዳለን። በምድር ላይ ቋሚ የሆነ ነገር የለም። ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ ይለዋወጣል። የማይለዋወጠው አንድ ነገር ግን ለውጥ የሚባለው ነገር ነው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜም ለሰው ልጅ ጊዜ(Season) ይሰጣል። ጊዜን ሲሰጥ ደግሞ ከጊዜ ጋር አብሮ ዕድልን ይሰጣል። ጊዜ እና ዕድል ሁሌም የማይነጣጠሉ እና አንዱ ከአንዱ ማይቀዳደሙ ነገሮች ናቸው።
እግዚአብሔር ጊዜን እና ዕድልን ሲሰጠን መጠቀም ካልቻልን እና ካባከነው ያንን ዕድል ደግመን ብንፈልገውም ላናገኘው እንችላለን። ጊዜ የሚባለው ጉዳይ በጣም ወሳኝ እና አንገብጋቢ ነገር ነው።
በልፋት፣ በጥረት እና ብዙ በመሞከር የሚመጣ ነገር የለም። እርግጥ ጠንክሮ መስራት እና መዘጋጀት መልካም ቢሆንም ሁሉም የሚሆነው ግን በእግዚአብሔር ጊዜ እና አቆጣጠር መሰረት ነው።
አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም፤ አጋጣሚ የሆነው ለእኛ እንጂ ነገሩ ሰማይ አቅዶበት የሰራው ነው። ጊዜንም ሆነ ዕድልን የሚሰጠው እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች እድል በሚሉት ነገር የሚመጣ ነገር ዕድል የለም። እግዚአብሔር የሚሰራው በጊዜ ውስጥ ነው። ያንን ጊዜ ማወቅ እና መረዳት እንዴት ያለ ዕድለኝነት ነው።
ስለ ጊዜ ማወቅ ያለብን 3 ነገሮች
1.ጊዜ ለአንዱ ሲሰጠው ከአንዱ ይወሰድበታል። ከሳዖል ጊዜ ሲወሰድበት ለዳዊት ደግሞ ያ ጊዜ ተሰጥቶታል።
2.አንዳንዶች ጊዜን(Season) ይሰጣቸዋል። ልክ እንደ ኤልያስ እና ሙሴ ከእነሱ በፊት በዛ መንገድ የሄደ ባይኖርም አዲስ ጊዜ ይሰጣቸዋል።
3.አንዳንዶች ጊዜን(Season) ይቀበላሉ። ልክ እንደ ኤልሳእ ከኤልያስ፣ ኢያሱ ከሙሴ እንደተቀበሉት ከእነሱ በፊት ካሉት ሰዎች እንደ ዱላ ቅብብል ጊዜን ይቀበላሉ።
እንግዲህ ጊዜ እንደዚህ ከሆነ ጊዜን ተቀባይ አልያም ጊዜ ሚሰጠን እንጂ ሚወሰድብን እንዳንሆን የእግዚአብሔርን ጊዜ ነቅተን እየጠበቅን እንዘጋጅ። ሪቫይቫል በደጅ ስለሆነ በዛ ሪቫይቫል ተካፋይ ለመሆን አሁን በሚገባ እንዘጋጅ። ኢየሱስ ይመጣል!!!!
Join us on
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
119 viewsJehovah jireh, 11:27