Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 1 እግዚአብሔርን በአቅሙ ልክ ካየነዉ፥ ያልተፈጠሩ ግዙፍ ሰማያትንና ምድርን በማየት፥ ልንለ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

ክፍል 1

እግዚአብሔርን በአቅሙ ልክ ካየነዉ፥ ያልተፈጠሩ ግዙፍ ሰማያትንና ምድርን በማየት፥ ልንለካዉ የምንሮጥበትን መንገድ፥ "ከንቱ!" ብለን ከዘጋን፥ እንግዳዉስ በክርስቶስ ስጋ በኩል፥ መርቆ በከፈተልን መንገድ፥ እንደ አብረሃም ወደ ሞርያን ምድር ይወስደናል፤ እንዴትና ለምን?

እንግዲህ አብረሃም በሕይወት አለና "እነሆኝ!" ሊል ቻለ፥ ታዲያ ሰዋ ከሚለዉ ቃል በላይ የቀደመችዉን የሞርያ ምድር አብረሃም እንዲያስባት ተፈለገ፥ እንኪያስ እግዚአብሔር ከወደዳቸዉ ከሺ ተራራዎች በአንዲቷ ላይ ለአብረሃም ቀጠሮ ተያዘለት፥ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

"ሞርያን" ማለት የፍጥረት መጀመሪያ፥ (የመሰረት ዲንጋይ)፥ ወይም የተራራዉ ቤተመቅደስ የሚል ፍቺ ይይዛል፤ እናም እግዚአብሔር አብረሃምን ሂድ እያለዉ ያለዉ፥ ሕይወት ወደሚገኝበት ምድር ነዉ ማለት ነዉ፤ ወዳጆቼ! ይስሃቅን በመስጠት ዉስጥ የመስዋቶቹን ቁሳቁስ በእጃችሁ ቢገኙም እንኳን፥ እግዚአብሔር እያወራዉ ያለዉ በፍጥረት ጅማሬ መንፈስ ነዉ፤ ሰዉ እግዚአብሔር ካሳየዉ ተራራዎች ይልቅ፥ በራሱ የሃሳብ ከፍታ ላይ ተራራዉን ገንብቶ፥ ለማመን ይከብደዋል፤ ይሄ ደግሞ፥ ሰዉ በእንቆቅልሽ እየወጣ፥ በደስታ የሚወርድበትን ፈንጠዝያ ይፈጥርበታል እንደማለት ነዉ፥
ስለዚህ የፍጥረት መነሻ ወደሆነዉ ቦታ ሲያመጣን ክርስቶስን እያስተዋወቀን ነበር ማለት ነዉ!

     @wisdom3in1