Get Mystery Box with random crypto!

“ኢየሱስንም፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።” — ሉቃስ 23፥42 እጅግ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“ኢየሱስንም፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።”
— ሉቃስ 23፥42

እጅግ ልብ ከሚነኩ ሕያዉ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መካከል ይሄ አንዱ ነዉ፥ ክርስቶስ ያለጠበቃና ያለምህረት፥ በምድር ፊት በእኛ ሁላችን መካከል ኋጥያትን ተጋፈጠ፤ በእርግጥ አመፅ መግደል ይችላል!፥ ሞትም ቢሆን ተሸንፎ አያዉቅም ነበርና ያቅራራል!፥ ብዙ ስሞች በክርስቶስ መስቀል ምክንያት፥ ሲጠብቁት ለነበረዉ አጋጣሚ፥ ነጥረዉ ለመዉጣት በአሸዋ ላይ ተተክለዉ ነበር፤ ወንበዴዉ ግን ዘወር ብሎ፦ ከነበሩት በሚጠይቀዉ ጥያቄ ንግግሩ ያስታዉቅ እንጂ፥ እንደዉም አስቀድሞ ቁርጡን ያወቀ ሰዉ ነበር፤ እዉነቴን ነዉ የምላችሁ!፥ በመቋጫዎች ላይ ሕይወትን ሊቀጥል የሚችለዉን ጌታ፥ መስቀል ላይ ይፈልግ ጀመር፤ በእርግጥ ይሄ ሰዉ እኮ ከነብያት መካከል አንዱም አይደለም!፥ ነገር ግን የሰዉ ምህረት የዘለለዉ ወንበዴ ነበር!

ወዳጆቼ የትኛዉም ነገር ከክርስቶስ ጋር ተካፋይ ላለማድረግ የነበረዉ አቅም ወደ እግዚአብሔር መንግስት በመግባታችን ተጠናቋል፥ ቀላል ሊመስላችሁ ይችላል!፥ ግን ደግሞ በስራዉ ረክሶ በቃሉ የጸደቀዉ ይህ ሰዉ፥ መምህሩን፦ "አስበኝ!" አለዉ፤ የነበረዉን ጊዜ ተጠቀመ!

የመጨረሻ ብዬ ልጨርስ፦ ክርስቶስ ኢየሱስን በተለየ መረዳት፥ ግን ተራ በሆነ የሰዉ ታሪክ ዉስጥ ማወቅ፥ ጩኋት ብቻ ከሆኑ ድምጾች በላይ ፍፃሜን ይወስናል!
አሜን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!