አንድ በእድሜ ገፋ ያለ ሽማግሌ ለሚስቱ ለሊት ላይ የማንኮራፏቷ ድምፅ አስቸግሮት ስሞታ ያቀርብላታል ። ሚስቱም እኔ የለብኝም ብላው ትክድ ነበር ። ይህ ነገር ሲደጋገምበት አንድ ለሊት ላይ ሆን ብሎ ይጠብቅና ለንግግሩ እውነታ ማስረጃ እንዲሆንለት ስታንኮራፋ ለመቅረፅ አሰበ ። እንዳሰበውም ቀረፀና አስቀመጠው ። ሌቱ ሲነጋ እሷ ተኝታ ነበር የቀረፀውን ሊያሳያት ይቀሰቅሳታል ። እሷ ግን የመጨረሻ ለሊቷ ስለነበር መነሳት አልቻለችም ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያቺ የማንኮራፋቷ ድምፅ ማታ ማታ ሁሌም ልክ እንደ አዝካሩን-ነውም እየደጋገመ ይሰማታል ። ----------------------------- ๏ ከቅርብ ወዳጅህ የሚመጣብህን ችግር ቻለውና እለፈው ምናልባት ይህ ችግር አለኝታ እንዲሆንልህና ያንን ሰው ከጎንህ እንዳታጣው የምትመኝበት ጊዜ ሊመጣ ይችላልና ። join join join @wexat_ena_islam 607 viewsye zd Lij, 18:30