Get Mystery Box with random crypto!

እኔም የለሁም እነሱም የሉም። ትላንት ያለነሱ ኑሮ መቃብር ይመስለኝ የነበረው...... ትላንት ከ | ንቁ ትውልድ

እኔም የለሁም እነሱም የሉም።

ትላንት ያለነሱ ኑሮ መቃብር ይመስለኝ የነበረው......
ትላንት ከኔ እንደሚርቁ ለደቂቃ እንኳን ማሰብ ከሞት በላይ የሚያስፈራኝ......
ትላንት መራቃቸውን ማሰብ ቃል ከሚገልፀው በላይ ህመም የሆነብኝ......
ትላንት በመኖራቸው ስለደመኩ ዛሬሜ ነገም ሁሌም አብሬያቸው ምደምቅ የመሰለኝ......
ውዴታዬ ጥግ ደርሶ ሰዎች ይታዘቡኝ የነበረው.....
ማን ቢሉኝ እነሱ ወዴት ቢሉኝ ወደነሱ እንዳላልኩ.....
ሰው ሲባል ካለነሱ የማይታየኝ አብሬያቸው መሆኔ ከጨረቃ በላይ ደምቄ ምታይ እንዳልመሰለኝ.......
..............................................................
ትላንት እስከዛሬ አንተን አለማወቄ ይፀፅተኛል ያሉኝ...
ትላንት መብላት መጠጣቴን ሁሉ ነገሬን ተቆጣጣሪዎቼ.....
ትላንት ምንም ቢመጣ ከጓንሽ ነን ያሉኝ.....
ትላንት አደለም ከፍቶኝ ፀሀይ መቶኝ እንኳን ፊቴን ጨፍገግ ካደረኩ ለኔ ይሁን ያሉኝ.....
ያለኔ ማንም ምድር ላይ የሌለ ያህል የወደዱኝ.....
ህመሜ ከኔ በላይ ያመማቸው ደስታዬ ከኔ በላይ ያስደሰታቸው የነበሩ .....
ሁሉም የሉም..... እኔም የለሁም.....ከነሱጋ የለሁም.....ከእኔጋር የሉም..... ሸሽተውኝ ወይስ ሸሽቻቸው ..... እንጃ እኔንጃ ብቻ እኔም የለሁም እነሱም የሉም።

ብቻ
በህይወቴ ምልልስ ውስጥ
ከዚበፊት የነበራቹ አሁን የሄዳቹ ....
አሁን አብራቹኝ ያላቹ ወደፊት ምትሄዱ .....
ወደፊት ምትመጡ ደግሞም ለምትሄዱ.....
ያለ ስስት ወዳቹሀለው

join join join

@wexat_ena_islam