Get Mystery Box with random crypto!

ተናገሪ ብዬ አላስገድድሽም..... ከአፍሽ ቃል ባትተነፍሺ አይኖችሽ ሁሉን ይነግሩኛል...... ተስ | ንቁ ትውልድ

ተናገሪ ብዬ አላስገድድሽም..... ከአፍሽ ቃል ባትተነፍሺ አይኖችሽ ሁሉን ይነግሩኛል...... ተስፋ እና ብርታት የሚሆኑኝ እነሱ ናቸው.....

እኔ ግን ለጆሮሽ ባይደርስም ልናገር....ቃል ልተንፍስ.... ቢሳካልኝ የጀነት ሙሽራዬ አንቺው ነሽ እንኩአንስ የዱንያ...... እኔን የከበደኝ አላህ ላገራለት ቀላል..... ኒእማውን ላደለው ደግሞ ስጦታ መሆኑን አውቃለሁ......

በእያንዳንዱ ሶላቴ መቁዓጫ ምን አንደምል ልንገርሽ.... ያረቢ የልቤ ማረፊያ ሆናለችና የቤቴ መድመቂያ...., የሕይወቴ ቅመም.... እስከጀነትም ተሻጋሪዬ አድርገህ አፅድቅልኝ..... አሚን! እላለሁ ለራሴ ካቀረረ እምባ ጋር ....... አይኖችሽ የሚሰጡኝን ብርታት...... የሚገልፁልኝ ፍቅር..... በአንደበትሽ ይሁኝታ አጅቢልኝ....... እባክሽ.....

አንቺን የምወድበት እኔነት ምንም ቢፈጠር ካንቺ ጋር ከመሆን የማያግደኝ ሆኖ ሳገኘው..... ያንቺ እኔን መውደድ በዛ ልክ መሆኑ አያጠራጥረኝም....... ፍራቻና ፍርሃትን ፍቅር በልጦ እንደሚያሸንፍ ታውቂ የለ?..... አትራቂኝ..... መራመድ ስትጀምሪ በብዙ እቀርባለው.........

መግለፅ አለመቻል..... መስማት የሚፈልጉትን አለመስማት ያማል..... ቢሆንም ትግስቴ ብዙ ነው..... ተስፋዬ ደግሞ ፈጥሮ የማይረሳኝ..... የጠየኩት የኔ ከሆነ ከማይነሳኝ ጀሊሉ ላይ......le hubi

•┈┈•••┈┈• •┈┈•••┈
  join join join

@wexat_ena_islam