Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው እባብ በእሳት ተቃጥሎ ሊሞት ሲል! ከእሳት ሊያወጣው ወሰነ! እያወጣው ባለ ግዜም ነደፈው | ወርቃማዎች

አንድ ሰው እባብ በእሳት ተቃጥሎ ሊሞት ሲል! ከእሳት ሊያወጣው ወሰነ! እያወጣው ባለ ግዜም ነደፈው በነደፈውም ጊዜ እራሱን ለማዳን ሲወራጭ እባቡ ተመልሶ እሳት ውስጥ ወደቀ ሰውዬው ለዛ አዘነ... እና እሳቱ ውስጥ የወደቀበት ምክንያት እሱ እንደሆነ አሰበ! እናም ሰውየው በቀኝ እና በግራ ዙርያውን ተመለከተ!

የብረት ዘንግ አግኝቶ ተጠቀመበት! እባቡን ከእሳቱ ለማውጣት እናም የእባቡን ህይወት አዳነው ይህን ሲያደርግ አንድ ሰው እያየ ነበር ከዚያም ወደ ሰውዬው ቀረበና፦ ይህ እባብ ነድፎሀል፣ ለምን ልታድነው ፈለክ? ብሎ ጠየቀው ሰውየውም መልሶ፦ የእባቡ ተፈጥሮ ቆሻሻ ነው! ይህ ግን ምህረት እና እርዳታ የሆነውን ተፈጥሮዬን አይለውጠውም!!! በማለት መለሰ!!

#አንድ_ሰው ስለ ጎዳህ ብቻ #ተፈጥሮህን እና #ሰብዐዊነትህን በቀላሉ አትቀይር! ሁል ግዜ ክፋትን በደግነት መልሰው!

@Werkamaa
@Werkamaa
@Werkamaa