Get Mystery Box with random crypto!

የታክሲ ገጠመኜን እንኩማ የው ሩቅ ተጓዥ ነኝ .... በቲኒሹ ታክሲ ውስጥ 1 ሰዓት እቀመጣለሁ . | ወርቃማዎች

የታክሲ ገጠመኜን እንኩማ

የው ሩቅ ተጓዥ ነኝ .... በቲኒሹ ታክሲ ውስጥ 1 ሰዓት እቀመጣለሁ .... ከዛም በላይ

አንዲት ጠይምዬ ቆንጅዬ ቲኒሽዬ/አስራዎቹ/ የሆነች ልጅ አጠገብ 3ተኛ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ .... በእጇ ፌስታል ምናምን ይዛለች

ወደ ጥግ አሳለፈችኝ

ቲኒሽ እንደተቀመጥን ስልኬን አውጥቼ ደዋወልኩና እዛው እጄ ላይ እንደያዝኩት ጉዞ ጀመርን

ስልክ አስደውዪኝ አለችኝ

እሺ እንኪ /ከፍቼ ሰጠኋት/

የደቡብ ልጅ መሰለችኝ ቋንቋዋን መለየት አልቻልኩም ደቡብዬ መሆኗ ግን እርግጥ ነው

ላውድ አድርጋ ደወለች ለአንድ 3 4 ደቂቃ አወራች ተዘጋ

እጄን ዘረጋሁ ስልኬን ልቀበል .... እሷ ወይ እቴ ሌላ ቁጥር መምታት ጀመረች ቅር አልተሰኘሁም አጠገቧ ነው ካርዱን የሞላሁት .... ካርድ አለው ብላ ስላሰበች ነው ፈታ ብላ ምትደውለው ብዬ ፊቴን አዞርኩላት

ከሁለተኛው ጋር የሚያወሩበት ደቂቃ ሲረዝም ቆይ ልደውልልሽ ብሏት መሰለኝ/የው ቋንቋውን ስለማይገባኝ ገምቼ ነው/ ዘጉ። አሁን ጨረሰች ስል መልሶ ደወለ እኔና ስልኬ ለረዥዥዥም ደቂቃዎች ተለያየን ..... አያልቅ የለ ተዘጋ

አሁን በቃሽ አይነት አስተያየት እያየኋት እጄን ዝርግት

ቆይ አንዴ አለችኝ የምታምረዋን ፈገግታዋን እያሳየችኝ በተሰባበረ አማርኛ

ፊቴን ወደ መስታወቱ አዙሬ ሳቅኩ .... ቲኒሿ እህቴን መሰለችኝ .... በቃ እኔን እህቷ አድርጋ በልበ ሙሉነት ስልኬን መያዟ .... ምንም አትለኝም የሚል እምነቷ እህቴ ናት ማለቷስ አይደል?

ነፃነቷ ገረመኝ .... የዋህነቷ አስቀናኝ .... የከተማ ሰው ልቡ በብዙ አጠራጣሪ ነገሮች መሞላቱን ያልተረዳች አዲስ አበባን በብዙ ያላወቀቻት መሆኗ ገባኝ ..... ለሶስተኛ ሰው ደወለች

ወላሂ ሳቋ ጨዋታዋ አይደለም የሰው ስልክ የያዘች .... በታክሲም የተሳፈረች አትመስልም .... ደስ አለችኝ ... ምን አባቱ ትጨርሰው ይሄን የዋህነቷን ልነጥቃት አልፈለግኩም .... ደስ እንዳላት እንድንለያይ አሰብኩ ... ስልኬን ረሳሁላት

አታምኑኝም አራተኛ ተደወለ

ይሄ ደውል የመጨረሻ ነበር .... እንኪ አናግሪያት አለችኝ

ሔለው
አቤት
እናት እንደው አደራ ጀሞ ሚካኤል ጋር ስትደርስ ንገሪያት .... እሷ ስለማታውቅ ነው .... አደራ እሺ ብረቱ ጋር ማደያው ጋር አውርጂያት
እሺ እማ እሺ ደርሰናል ቲኒሽ ነው የቀረን .... (መውረጃዋ ጋር ልትደርስ አንዲት ፌርማታ ሲቀራት ነበር ስልኬን የሰጠችኝም አሳያት የተባልኩትም)

አመሰግናለሁ አለችኝ .... ልብን ደስ ከሚያሰኝ ፈገግታዋ ጋር

የዋሆችን አኑርልን
@WERKAMAA