Get Mystery Box with random crypto!

ደስስስስ ይለኛል ..... ደግሞ ይቀጥልና ደስም አይለኝም .... እሰለቻለሁ .... በረታለሁ . | ወርቃማዎች

ደስስስስ ይለኛል ..... ደግሞ ይቀጥልና ደስም አይለኝም .... እሰለቻለሁ .... በረታለሁ ..... አለቅስ አለቅስ .....አለቅስና እያለቀስኩ እስቃለሁ ..... ሳቄ አልቅሼ ማላውቅ ያህል እስኪሆን ..... ስከፋ ተደስቼም ስቄም ማላውቅ ያህል የሆነ !

ወዳለሁ ! ፍቅር ክንፍ እስኪያደርገኝ ..... እብድ ንድድ ጭስስ እስክል እወዳለሁ .... እማረካለሁ ስለ-ፍቅሬ ስለ-ውዴታዬ እዬዬን አክላለሁ ...... ማፍቀርን መውደድን የመሰለ ወይን እጎነጫለሁ ..... አጣጥማለሁም

ይደግም ይደግምና ....... ጥላቻ ይይዘኛ ..... የሚያስጠላኝ ያስጠላኛል ..... ጥልት ጥልትልትትትት አድርጌ ጠላለሁ ..... በልቤ ስር ፍቅር ዘሩን ዘርቶ ማያውቅ መስል እጠላለው ..... እስጥልት አድርጌ ጠላለሁ ...... መጠላላትን እስክጠላ ጠላለሁ .... ጥላቻዬንም ጠላዋለሁ

ሰው የመሆን ቅኔዬ .... በአንድ ዓለም ብዙነቴ ..... በአንድ ልብ ብዙ ማንነት .... የትናንት የዛሬ የነገ ሁነት .... ሁሉም እኔ'ነት ..... እኔም ሁሉነት .... ሰውነቴ
@WERKAMAA