Get Mystery Box with random crypto!

UFO (Unidentified flying object) ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት) ክፍል ፮ በ | አስትሮኖሚ ኢትዮጵያ 📡

UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል ፮

በውጊያ ስልት ከፍተኛ ልምድ የነበራቸው የታላቁ እስክንድር ወታደሮች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 329 ዓመተ ዓለም የግሪክ ጦር የጃክሳርቱስ ወንዝን አልፎ ወደ ህንድ ሲገባ መንገዳቸውን ያቋረጠውን የUFO ስብስብ "ትላልቅ ብርማ ተብረቅራቂ ጋሻዎች" ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 384--322 ዓመተ ዓለም የኖረው አርስቶትል የግሪክ ስፖርተኞች የሚወረውሩትን ዲስክ ያውቅ ስለነበር እነዚህን ባእድ አካላት "የሰማይ ዲስኮች" ብሏቸዋል። ሮማውያን ልክ እንደታላቁ እስክንድር እንደጋሻዎች ወይም የእሳት ጦሮች ወይም የመርከቦች ስባስብ አድርገው ያዩአቸው ነበር። ፕሊኒ የተባለው ጸሃፊ 'ናቹራል ሂስትሪ' በተባለው መጽሃፉ ሁለተኛው ቅጽ ላይ እንደሚከተለው ጽፏል። «በሉሲየስ ቫሌሪየስ እና በጊየስ ቫሌሪየስ እማኝነት የእሳት ፍንጥቅጣቂ በሁሉም አቅጣጫ ይረጭ የነበረ የሚነድ ጋሻ በፀሃይ መጥለቂያ ጊዜ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ በሰማዩ ላይ እየትወረወረ ሄደ»።
በአዳዲስ ነገሮች መፈልሰፊያና በዓለማት ፍለጋ ዘመን እነዚህን በራሪ አካላት ያዩ ሰዎች ከመርከቦች ጋር አመሳስለዋቸው ነበር። በኋላም ተንሳፋፊ ፊኛዎች በተፈለሰፉ ጊዜ እነዚህ በራሪ አካላት ፈረንሳይ ውስጥ እብረቅራቂ የእሳት ፊኛዎች ተብለው ተገልጸዋል። በ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ቨርሞንት ውስጥ እነዚህን ነገሮች ያዩዋቸው ሰዎች የዘንግ ቅርፅ ያላቸው የአየር ላይ ተሽከርካሪዎች ብለው ገልጽዋቸዋል።
.
.
.
.
ይቀጥላል
@ethioastronomy
@universeone123