Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅረኛዬ ፈተና ወደቀች በሚል ትምህርት ቤቱን ያቃጠለዉ አፍቃሪ በግብጽ ሜኑፊያ ግዛት ነዋሪ | Ministry of education®

ፍቅረኛዬ ፈተና ወደቀች በሚል ትምህርት ቤቱን ያቃጠለዉ አፍቃሪ

በግብጽ ሜኑፊያ ግዛት ነዋሪ የሆነዉ የ21 ዓመት ወጣት ፍቅረኛዉ የነበረባትን የትምህርት ፈተና ማለፍ ባለመቻሏ ትምህርት ቤቱን በእሳት አጋይቷል፡፡የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደገለጸው በእሳት አደጋዉ የሞተ ሆነ የተጎዳ ሰው የለም ብሏል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እጮኛው የትምህርት ቤቱን ፈተና መዉደቋ ክፍል እንድትደግም የሚያስገድዳት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰርጋችንን ቀን ይገፋብናል ሲል ተናግሯል። ድርጊቱን ከፈጸመ በኃላ ከአካባቢዉ ተሰዉሮ የነበረ ሲሆን የዓይን እማኞች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፍ ዴሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER