Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ | Ministry of education®

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የፈተናው ቅድመ ዝግጅት ሥራ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን አካላት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER