Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ የአማራ ክልል ህብረተሰብ | TIKVAH-MAGAZINE

በአማራ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት በክልሉ ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን ገለፀ።

ባለፈው ሳምንት ብቻ 7ሺህ ሰዎች የወባ ምርመራ አድርገው 2ሺህ 460 ሰዎች በሽታው መያዛቸው ተነግሯል።

በክልሉ ያለው ግጭት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን እንዳዳከመው የክልሉ ጤና ተቋማት ኃላፊዎች መግለፃቸውን ዶይቼ ቬለ በዘገባው አመልክቷል።

ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተኛ ግንዛቤና ቸልተኝነት ችግሩ እንዲባባስ ምክንያት መሆኑንም ነው ሀላፊዎቹ የገለፀት።

#አማራክልል   #ወባ     #ጤና

@TikvahethMagazine