Get Mystery Box with random crypto!

በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? 'ኢዱኬሽን ፈርስት' | TIKVAH-MAGAZINE

በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

"ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል።

ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው።

በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦

ደቡብ አፍሪካ
ኬንያ
ናይጄሪያ
ጋና
ኡዳንዳ መሆን ችለዋል።

ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች።

2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።

@TikvahethMagazine