Get Mystery Box with random crypto!

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች ላይ ያተኰረ ኢንሳይክሎፔዲያ ሊዘጋጅ | TIKVAH-MAGAZINE

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች ላይ ያተኰረ ኢንሳይክሎፔዲያ ሊዘጋጅ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች እንዲሁም አስተምህሮዎች ላይ ያተኰረ መዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፔዲያ) በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት ሊዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል።

የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ በዛሬው እለት በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

የሚዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፣ ጥንታዊና ሐዋርያዊ አስተምህሮ ፣ ዶግማ ፣ ቀኖና እና ትውፊት እንዲሁም የጳጳሳትን፣ የሊቃውንትን፣ የትልልቅ ገዳማትንና አድባራትን ታሪክ ወዘተ የሚያካትት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት በዘገባው አመልክቷል።

@TikvahethMagazine