Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቆማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመጪው ክረምት የስልጠና መርሃ ግብር የሚ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመጪው ክረምት የስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ምዝገባ ጀምሯል። በስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ እና ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።

በመጪው ክረምት ለተከታታይ ሁለት ወራት ለሚሰጠው ስልጠናም ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቋል። ስልጠናው ከሚያተኩርባቸው መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ሮቦቲክስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል።

በዚህም ስልጠናው መሳለፍ የምትፈልጉ አመልካቾች በሊንክ 1 እንዲሁም በሊንክ 2 ላይ ያሉትን የመመዝገቢያ ቅጾች በመሙላት እንድትመዘገቡ ጥቆማ ቀርቧል።

@TikvahethMagazine