Get Mystery Box with random crypto!

#Update: በአማራ ክልል ጃማ እና ወረኢሉ ሰብላቸው በዋግ ለተጠቃ 51 ሺ አርሶ አደሮች 39 ሚ | TIKVAH-MAGAZINE

#Update: በአማራ ክልል ጃማ እና ወረኢሉ ሰብላቸው በዋግ ለተጠቃ 51 ሺ አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር ካሳ ተከፈለ

የኦሮሚያ ኢንሹራንስ በሰብል መድህን ፕሮግራም በአማራ ክልል ጃማ እና ወረኢሉ በቢጫ ዋግ ሰብላቸው ለተጠቃ 51 ሺ 132 አነስተኛ አርሶ አደሮች 39.4 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉ ተገለፀ።

ክፍያውን በኦሮሚያ ኢንሹራንስ ሲከፈል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI)፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) እና ፑላ አድቫይዘርስ (Pula) በጥምረት የሰብል መድህን የካሳ ክፍያ ስነ ስርዓቱን በዛሬው እለት አከናውነዋል።

እነዚህ አርሶ አደሮች በፀደይ ባንክ በኩል በገዙት  ማዳበሪያ አማካኝነት የኢንሹራንስ ተጠቃሚ መሆናቸው ሲነገር የኦሮሚያ ኢንሹራንስ የፕሮግራሙን ጨረታ በማሸነፍ ክፍያውን ፈፅሟል። በቀጣይ ሌሎች የሰብል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንዲሆኑና በ3 ክልሎች 1 ሚሊየን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ተብሏል።

@TikvahethMagazine