Get Mystery Box with random crypto!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ | TIKVAH-MAGAZINE

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት የኢድ አል ፈጥር እና መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

በዚህም፦

በሙሉ ይቅርታ ወንድ 637 ፤ሴት 11 ፤

በልዩ ሁኔታ ወንድ 3 ሴት 3

በጠቅላላው 654 ታራሚዎች ሲሆኑ ለ 4 ወንዶች ደግሞ የእስራት ቅናሽ ተደርጎላቸዋል።

በክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ስር ባሉ #ሰባት ማረሚያ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች በ2016 በጀት ዓመት ይቅርታ ሲደረግ ይህ ለ2ኛ ዙር ነው።

@TikvahethMagazine