Get Mystery Box with random crypto!

በአለም ተወዳጁ የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ መገኘቱ በጥናት ተረጋገጠ | TIKVAH-MAGAZINE

በአለም ተወዳጁ የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ መገኘቱ በጥናት ተረጋገጠ

በአለም ተወዳጅነትን ያተረፈው የአረቢካ ቡና ዝርያ ከ600,000 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ደኖች ውስጥ በሁለት ሌሎች የቡና ዝርያዎች ተፈጥሯዊ ውህደት ስለመፈጠሩ ዓለማቀፍ የሳይንስ ተመራማሪዎች ቡድን በጥናት ማረጋገጣቸውን በኔቸር ጄኔቲክስ ላይ የወጣው የምርምር ውጤት ያመላክታል።

ይህ የአረቢካ ቡና ተክል መነሻው ኢትዮጵያ ሲሆን ተመራማሪዎች የዚህን የቡና ተክል የጂኖሚክ መረጃን በመጠቀም የቡናውን የረዥም ጊዜ ታሪክ ለማጥናት እና በዘመናዊ መንገድ ከሚመረቱ  ሌሎች የቡና ተክሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለመለየት ጥናት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም የአረቢካ ቡና ከ "Coffea canephora" እና " Coffea eugenioides "  ከተባሉ የቡና ዝርያዎች ከእያንዳንዳቸው ሁለት ክሮሞዞሞችን በመውሰድ ከ600ሺ አመታት በፊት ስለመፈጠሩ የሳይንስ ተመራማሪዎቹ በተጠቀሙት የጊዜ ስሌት ቀመር ማረጋገጣቸውን ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine