Get Mystery Box with random crypto!

ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ስርዓትን ለማሳለጥ ይረዳል የተባለው COMESA ተግባራዊ ሊደረግ ነው። ኢ | TIKVAH-MAGAZINE

ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ስርዓትን ለማሳለጥ ይረዳል የተባለው COMESA ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

ኢትዮጵያ የፈረመችው እና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችለው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(COMESA) ቀጠናዊ የጉምሩክ ዋስትናን ለመተግበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተገለጸ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የትራንዚት እና መጋዘን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወጋየሁ አዳሙ፣ ቀጠናዊ የጉምሩክ ትራንዚት ዋስትና ከዚህ በፊት በየሀገራቱ የሚደረገውን ተደጋጋሚ የእቃ ዋስትና የሚያስቀር እና እቃዎች በአንድ ዋስትና ብቻ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል አሰራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"ኢትዮጵያን ጨምሮ በ13 አባል ሀገራት መካከል የተፈረመው አዲሱ የጉምሩክ ትራንዚት ዋስትና ወጭዎችን የሚቀንስ፣ የትራንዚት ጊዜን የሚያሳጥር፣ የእቃ አወጣጥ ሂደቶችን የሚያፋጥን በአጠቃላይ ፈጣን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል ነው“ ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

አቶ ወጋየሁ አክለውም፣ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ እና ከጉምሩክ የመረጃ ቋት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ ለጉምሩክ አስተላላፊዎች ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡

ቀጠናዊ የጉምሩክ ዋስትናን ለመተግበር ከኢንሹራንስ፣ ከባንኮች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ የሆኑ ውይይቶች እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡም መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine