Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወሰነ። በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው | TIKVAH-MAGAZINE

የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወሰነ።

በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ላለፈው አንድ ወር ጥናት ሲደረግ ቆይቶ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ቀለማቸው ግራጫ ቀለም ያላቸው መሆኑን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ለማሳያነት የጠቀሱት ኃላፊው፣ በቂርቆስ ከ100 ሕንፃዎች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ ነው ብለዋል፡፡ ከእዚህ ውጪ ያሉት ቀለሞች አነስተኛ ቁጥር ያላቸውና የተለያዩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

‹‹መሬት ላይ የሌለ አዲስ ቀለም ብናስቀምጥ የተሠሩት ሁሉም ሕንፃዎች እንደ ገና [ቀለም] ሊቀይሩ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዋነኛው የትኛው ቀለም ነው የሚለውን ወስደን ቀሪዎቹ ሕንፃዎችና ወደፊትም የሚሠሩት በተመሳሳይ ግራጫ እንዲሆኑ ወስነናል፤›› ሲሉ ለከተማዋ ሕንፃዎች ግራጫ የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ግራጫ ቀለም ሲወሰን ሁሉም ሕንፃዎች ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ ቀለም ይኖራቸዋል ማለት እንዳልሆነ የሚናገሩት ኃላፊው፣ እስከ 30 የሚደርሱ በኮድ የሚለያዩ የግራጫ ቀለም ዓይነቶች እንዳሉና የሕንፃ ባለቤቶች ከእነዚህ ውስጥ መምረጥ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከግራጫ ቀለም ዓይነቶች ውስጥ የማይካተት ቀለም የተቀቡ ሕንፃዎች በሙሉ፣ ቀለማቸውን በግራጫ ቀለም አማራጮች እንደሚቀይሩ አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለከተማዋ ሕንፃዎች የቀለም ስታንዳርድ ተግባራዊ የማድረግን ሐሳብ ከሳምንታት በፊት በተደረገው የከተማ አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አንስተው ነበር፡፡

Read more https://telegra.ph/ሪፖርተር-05-18

@tikvahethmagazine