Get Mystery Box with random crypto!

ባልታወቀ ምክንያት የተቋረጠው ከአርባምንጭ -ሻሸመኔ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሰኔ 1 ጀምሮ ይቀጥ | TIKVAH-MAGAZINE

ባልታወቀ ምክንያት የተቋረጠው ከአርባምንጭ -ሻሸመኔ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሰኔ 1 ጀምሮ ይቀጥላል ተባለ።

ባልታወቀ ምክንያት ተቋርጦ እንደነበር የተገለጸው ከአርባምንጭ -ሻሸመኔ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር የምዕራብ አርሲ እና የጋሞ ዞኖች ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በሰፊው በመወያየት ከሰኔ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎቱ ይጀምራል ሲሉ የምዕራብ አርሲ ዞን ትራንስፖርት ኤጀንሲ ተወካይ እና የትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጫ ሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ትቤሶ ሎሎ ተናግረዋል።

የጋሞ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሣይ ካሎሴ ከአርባምንጭ ወደ ሻሸመኔ የሚደረግ ከፍተኛ ፍላጎትና ፍሰት ያለው አካባቢ መሆኑን አስታውሰው የዞኑ መንግስት እንዲጀመር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine