Get Mystery Box with random crypto!

ደስታን ፍለጋ በግምት ወደ 50 ሰው የሚይዝ ህብረት በአንድ አዳራሽ ለጥብቅ ጉዳይ ይሰባሰባሉ::ፕ | ሰው መሆን...

ደስታን ፍለጋ
በግምት ወደ 50 ሰው የሚይዝ ህብረት በአንድ አዳራሽ ለጥብቅ ጉዳይ ይሰባሰባሉ::ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት መድረክ መሪው ታዳሚዎችን አንድ ጫወታ ሊያጫውት ይወስናል::በአዳራሹ ለተሰበሰቡ ሰዎች አንዳንድ ፊኛ ሰጥቷቸው ስማቸውን በእስክሪብቶ ፊኛው ላይ እንዲፅፉበት ያዛቸዋል::
ሁሉም ፅፈው ከጨረሱ በሁዋላ ፊኛው ተሰብስቦ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ተበታትኖ እንዲቀመጥ ያደርጋል::በመቀጠል ጫወታው በ5 ደቂቃ ጠባቧ ክፍል ውስጥ ተበታትኖ ከተቀመጠው ፊኛ እያንዳንዳቸው ስማቸው የተፃፈበትን ፊኛ አግኝቶ መመለስ ነው ተባለ::በቅፅበት ያቺ ክፍል ስማቸውን በሚፈልጉ ታዳሚዎች ትርምስምስዋ ወጣ::ነገር ግን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ትዕዛዙን ተግብሮ ስሙን ያገኘ አንድ እንኳን አልነበረም::የጫወታው አስተባባሪም ከመድረክ ወጥቶ 1 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሀምሳዎቹም ፊኛቸው ስማቸውን እየጠራ መለሰ:: ደስታም እንዲህ ናት::በዚህች ጠባብ እና በማይሞላላት አለም ትውልድ ከሌላው ይልቅ የራሱን ደስታ ፍለጋ ይተራመሳል!!
ነገር የደስታን መገኛ በቅጡ አላወቀም::
አትጠራጠሩ በክፍሉ ውስጥ መጀመርያ ያገኙትን ፊኛ ለስሙ ባለቤት እየጠሩ ቢሰጣጡ ልክ እንደመድረኩ 1 ደቂቃ አይፈጅባቸውም ነበር::
ስለዚህ የእርሶን ደስታ ማግኘት ይሻሉ ??
የሌላ ሰው ደስታ በእጅዎ ነውና ይመልሱ ያን ጊዜ የእርሶ የሆነ ነገር ወደ እጅዎ ለመግቢያ ጊዜ አይፈጅም!!! መልካም ሌሊት ተመኘሁ


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni