Get Mystery Box with random crypto!

#በፍቅር_እንኑር መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል | ሰው መሆን...

#በፍቅር_እንኑር

መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል ትንፋሽ መውሰጃ ጊዜ የለም፡፡ምን አልባትም ማይክሮሰከንድ አይኖርም ይሆናል፡፡ነገር ግን ሽርፍራፊዋም ብትሆን ያው የኛ ዕድሜ ነች፡፡በዚህ ዓለም አረፍ የምንልባት(የምንኖርባት እንዳልል ከመጣንበት ዝንት ዓለም እና ከምንሄድበት ዘላለም አንፃር የዕድሜያችን ርዝማኔ መለኪያው ስለማይነፃፀር እና ከዓይን ጥቅሻ ያነሰ በመሆኑ ነው)አንዳአንዴ ያንኑው የጥቅሻ ዕድሜ ያሰለቸናል፡፡ያነጫንጨናል፡፡ምክንያቱም እንደማረፊያ ሳይሆን እንደ ቋሚ መኖሪያ እናስባታለን፡፡እናም ቋም ነገሮችን ለመገንባት እንጣጣራለን...ወደ ውስጥ የሳብነውን አየር መልሰን ወደ ውጭ ሳንበትን የረፍት ጊዜያችን ይገባደድ እና እረጂም..በጣም እረጂም የፀጥታ እና የማይታወቅ ጉዦችንን እንጀምራለን፡፡
እና የዘላለም ተገጓዦች ነን፡፡በምድር ምንገነባው ህንፃ ማረፊያ ድንኳን እንጂ ቋሚ ሀውልት አይደለም፡፡ዘና ብሎ መሳቅ ...በፈገግታ መደሰት እንጂ ፊታችንን አጨማደን… ልባችንን አኮማትረን ..ስለ ኒዩኪሌር ቦንብ መጠበብ በህይወት ስለት ትርጉመ ቢስ ነው
ህይወት እኮ ምትሰለቸን እረፍታችን ምቸት ስለሌለው ነው...ለዚህ ነው የሚቀነቅነን፡፡የአብዛኞቻችን ኑሮ በችግር የታጠረበት ዋናው ምክንያት የጥቂተች ስግብግብነት ነው፡፡መቶ ሺ ዓመት በዚህች ምድር እንደሚኖር ..አንድ ሺ ሰዎች እድሜ ልክ ማኖር የሚችን ንብረት ብቻውን ታቅፎ እና ቀብሮ...እሱ በምቾት እና በስግብግብነት ቅዠት ውስጥ እየኖረ ..ሌሎች ሺ ዋችን በችግር እና በሰቀቀን ቅዠት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ትርፉ ምንድነው፡፡
እና እስቲ እንተሳሰብ፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡ ጠብታ ጊዜያችንን በክፋት አናጨማልቃት፡፡በፈገግታ ጀምረን...በሳቅ አዋዝተን....በዜማ አጅበን...በደስታ ዘለን...በፍቅር ሰክረን..በእርካታ እንሰናበታት፡፤መጨረሻችን መድረሻ የሌለው ዘላለም አይደል፡፡
ስለዚህ መልካም አልመን ...መልካም ተግብረን...በመልካም ሁኔታ ኖረን..ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ፀፀት አልባ ሆነን እንድንገጓዝ ከፀለምተኛ አስተሳሰባችን...ከስግብግብ ባህሪያችን...ከመጠላለፍ ምግባራችን እንላቀቅ፡፡ትናንትን አክባሪ...ዛሬን አፍቃሪ...ነገን ናፋቂ እንደሆን ህይወትን ሳንሰለች ሩጫችንን በጥሩ አነሳስ ጀጀምረን በድንቅ አጨራረስ ማጠናቀቅ ይገባናል

#መልካም_ቀን

ከዘሪሁን

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni