Get Mystery Box with random crypto!

::::::::የቱ ነው ትክክል??????::::::::::: ለትክክለኛነት እና ለስህተተኝነት ጥያቄዎቻ | ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge

::::::::የቱ ነው ትክክል??????:::::::::::
ለትክክለኛነት እና ለስህተተኝነት ጥያቄዎቻችንን መልስ እንደመስጠት፤ ለእውነት እና ለሃሰት መለኪያችን መስፈርትን እንደማግኘት፤ ለማንነታችን  ትርጉምን እንደመፈልግ ህሊናን የሚረብሽ ምን ነገር አለ? ልብ እና አይምሮ ሲቃረኑ፤ እምነት እና ፍላጎት ሲጣሉ፤ ግለኝነትና ማህብረሰብ መስመር ሲለዩ ምን ማድረግ እንችላለን?በመንታ መንገድ ላይ ቆመው እንደመዋዥቅ ምን የሚያስጨንቅ ነገር አለ?

አንዳንዴ በውስጣችን ልክ የሚመስለንን ነገር እንዳናደርግ፤ ፍላጎታችንን እንዳንኖር፤ እውነተኛ ማንነታችንን እንዳናወጣ የሚያስፈሩን ብዙ ነገሮች አሉ። ልማድ እና የማህበረሰብ መስፈርት ዋነኞቹ ናቸው። ለምሳሌ በእውነተኛ ፍቅር ማንም ሰው ክርክር የለውም፤ ነገር ግን እውነተኛ ፍቅር በሚይዛቸው ሰዎች ላይ ግን ጥያዎች ይኖራሉ። በእድሜ የሚለያዩ ሰዎች ሲዋደዱ፤ በሃይማኖት የሚለያዩ ሰዎች ሲዋደዱ፤ በዘር የማይገናኙ ሰዎች በፍቅር ሲወድቁ፤ የእውነተኛ ፍቅር ትክክለኛነት በማህበረሰቡ ዘንድ ጥያቄ ወስጥ ይወድቃል።

ውሸትን እንውሰድ፤ የትኛውንም ሃይማኖት ብንከተል ውሸት ከሌሎች ሃጥያቶች እኩል ሃጥያት ነው። ነገር ግን ውሸት ቅዱስ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ ሰዎችን ከጥፋት ለማዳን ወይም ሰዎችን ለማስታረቅ እንዋሻለን። ታዲያ ትክክለኛ እና ስህተት የምንላቸው ነገሮች እንደየሁኔታው ይለያዩ ይሆን?