Get Mystery Box with random crypto!

'የምንሰጠውን ነገር ልብ በእንበል” ። እንካችሁ የምንለውን ጥበብ፤ ምክር፤ ፍቅርና እምነት እኛ ጋ | ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge

"የምንሰጠውን ነገር ልብ በእንበል”
። እንካችሁ የምንለውን ጥበብ፤ ምክር፤ ፍቅርና እምነት እኛ ጋር ብቻ ባለው ዋጋ ብንመዝነው፤ ለሰጠነው ሰው ዋጋው በዝቶ ሊያስደስተው ወይም አንሶ ሊያስከፋው ይችላል ፡፡
ለሰው እጅ መንሻ የገበርነው ግብር
እውቀት፤ ጥበብ፤ ፍቅር፤ ሙገሳና ክብር
ለእኛ ውድ ሆኖ እጅግ አግዝፈነው
ተቀባዩ እጅ’ላይ ፤ ተራ ኢምንት ሆኖ፤ ሲረክስ አየተነዋል!!!
ወርቅ ለተረፈው ወርቅ ሰጥተን እንዲገረም መጠበቅ ሞኝነት ነው ። ለእኛ ውድ የሆነው ነገር ለሌላውም ሰው ውድ እየመሰለን ስንቴ ተሸውደን ይሆን? ብዙ የምናውቅ መስሎን ከእኛ በላይ ለሚያውቅ ብዙ አውርተን፤ ከእኛ በላይ ለኖረ ስለኑሮ ሰብከን፤ ከእኛ በላይ ለታገለ ስለ ትግል አስረድተን፤ ከእኛ በላይ ለሚያምን ስለ እምነት ሞግተን፤ ወርቅ ለተረፈው ወርቅ ሰጥተን አናውቅም?