Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ትዕግስት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ጨርሶ በማታውቀው ምክን | ቅዱስ ድልድይ/kidus bridge

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ትዕግስት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጨርሶ በማታውቀው ምክንያት መኖርህን የሚፈታተኑ አበሳዎች ፤መከራወች፤ችግሮች ብዙ ናቸው፡፡ በየጊዜው ፊታቸውን እየለዋወጡ ይፋለሙሃል፤ያሳዝኑሀል፤ያስጨንቁሀል፤ያስለቅሱሀል:: ዘመንህን ሁሉ መከራን እያስተናገድክ “እንድትኖር” የተፈጠርክ ይመስል… ትበሳጫለህ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፤ነገን መናፈቅ ታቆማለህ፤ዛሬ ይሰለችሀል ፤ህልምህ፤ ዓላማህ፤ ምኞትህ ከሀሳብህ ብን ብለው ይጠፉብሀል...........ባላሰብክበት ሰዓት ድንገት ተንደርድረው በመምጣት ወደ ሞትህ የሚገፈትሩ ንዴትና ብስጭቶች ስሜትህ ውስጥ ብቅ፣ ጥልቅ ማለታቸውም አይቀርም
ያኔ ታድያ አትኩሮትህን ሁሉ ትዕግስት ላይ በመሰብሰብ፣ በውስጥህ የሚንፈራገጠውን አውሬ “እረፍ” ማለት መቻል አለብህ፡፡ ትዕግስት ራስን ከመረዳት ይወለዳል:: ራስህን ስትረዳ ስሜትህን መግራት አያዳግትም:: ያኔ ንዴትና ብስጭት በለኮሱት የእሳት ነበልባል በሚፈጠር ብርሃን አካባቢህን ለማየት ትችላለህ:: መቻል ከሙከራ፣ ሙከራም ተስፋ ካለመቁረጥ የሚገኝ በረከት ነው፡፡
...''እውነት ነው መኖር ለብዞወቻችን ፈተና ነው''....