Get Mystery Box with random crypto!

#ሊሞቱ_የደረሱ_ሰዎች_የሚቆጫቸው_10_ነገሮች #Ethiopia  | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይ | The Motivator

#ሊሞቱ_የደረሱ_ሰዎች_የሚቆጫቸው_10_ነገሮች

#Ethiopia  | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።

1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።

2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።

3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።

4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?

5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።

9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።

10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።

ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም።  ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል።

@the_motivators
@the_motivators