Get Mystery Box with random crypto!

#አትዋሽ_በፍጹም_አትዋሽ! ከፍ አድርገህ አልም፡፡ ትኩረት ይኑርህ፡፡ ማስተካከል የምትችለውን ነገ | The Motivator

#አትዋሽ_በፍጹም_አትዋሽ!

ከፍ አድርገህ አልም፡፡ ትኩረት ይኑርህ፡፡ ማስተካከል የምትችለውን ነገር አስተካክል፡፡ ባለህ እውቀት አትታበይ፡፡ ፍፁም የሆነ ኩራት ባለመቻቻል፣ በጭቆና፣ በማሰቃየት እና በሞት ስለሚገለጥ ትሁት ለመሆን ጥረት አድርግ።

የራስህን ብቁ አለመሆን፣ ፈሪነት፣ ተንኮለኝነት፣ ቂም እና ጥላቻ እወቅ።

ሌሎችን ከመክሰስህ በፊት እና የዓለምን ጨርቅ ለመጠገን ከመሞከርህ በፊት የመንፈስህን ክፋት ተመልከት። ምናልባት ጥፋቱ የዓለም ሳይሆን የአንተ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት አላማህን ስተህ ይሆናል፡፡ ምናልባት የእግዚአብሔር ክብር ጎድሎህ ይሆናል፡፡ ምናልባት ኃጢአተኛው አንተ ትሆናለህ፡፡

ሁሉም ለዓለም አቅም ማጣት እና የክፋት መስፋፋት ያደረግከው አስተዋፅኦ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

ከሁሉም በላይ በፍጹም አትዋሽ! ስለምንም ነገር በጭራሽ አትዋሽ፡፡ ውሸት ወደ ሲኦል ከሚመሩ ነገሮች መካከል አንደኛው ነው፡፡

@the_motivators
@the_motivators