Get Mystery Box with random crypto!

#ነጻ_እስክትሆን_ባሪያ_ሁን! ኒቼ አንድ ድንቅ ሃሳብ አለው - ስለ ነጻነት። እሱ እንደሚያምነ | The Motivator

#ነጻ_እስክትሆን_ባሪያ_ሁን!

ኒቼ አንድ ድንቅ ሃሳብ አለው - ስለ ነጻነት።

እሱ እንደሚያምነው "ባርነት" ባላደገው ሰውና በነጻው ሰው መሃል ያለ ነው። ነጻ ለመሆን መጀመሪያ ባርያ መሆን አለብህ።

ለተወሰነ ጊዜ ለማይለወጥ፣ ለማይቀየር ስነስርዓትም መገዛት ይኖርብሃል፤ ነጻነትህን እስክታውጅ ድረስ።

ለምሳሌ ፈረንሳይኛ ቋንቋን መማር ፈለግክ፤ ስትጀምረው ቀላል አይሆንም።
ምንም የምታውቀው የፈረንሳይኛ ቃልም የለም። ብዙ ሺ ነገሮችንም ማስታወስ ይጠበቅብሃል።

እንደ ጀማሪ ትኮላተፋለህ፣ ትሳሳታለህ፣ ትወድቃለህ፣ ትነሳለህ። እናም ያለህ ብቸኛ አማራጭ ራስህን ለስርዓት ማስገዛት ነው።

"ይህን አደርጋለሁ፣ በቀን ውስጥ ይህን ያህል ቃላትን..." እይዛለሁ እያልክ የማይለወጡ ህጎችን ታወጣለህ። ፈረንሳይኛ ቋንቋ እያንገሸገሸህ የምትማረው ሳይሆን ወደኸው የምታደርገው እስኪሆን ድረስ ነጻነትህን ለማግኘት ትታገላለህ፤ የመጨረሻ ግብህ የሚሆነውም ነጻነትህን ማግኘት ነውና።

ነጻ እስክትሆን ድረስ ባሪያ ሁን- ባሪያ ሆነህ ግን እንዳትቀር ተጠንቀቅ፡፡

@the_motivators
@the_motivators