Get Mystery Box with random crypto!

የቂያማ ቀን ቋሚ የችሎት ስርዓት ለቂያማ ቀን በሚዘጋጀው የፍርድ አደባባይ ላይ ከመቆማችን በ | አስ–ሱናህ

የቂያማ ቀን ቋሚ የችሎት ስርዓት

ለቂያማ ቀን በሚዘጋጀው የፍርድ አደባባይ ላይ ከመቆማችን በፊት ቦታው የሚኖረውን ድባብ በጥቂቱ ...

ያኔ ፋይሎች ሁሉ ሚስጢራዊ አይደሉም

ﻭﻧُﺨﺮِﺝُ ﻟَﻪُ ﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟﻘِﻴﺎﻣَﺔِ ﻛِﺘﺎﺑﺎ ﻳَﻠﻘﺎﻩُ ﻣَﻨْﺸُﻮﺭًﺍ

"በዕለተ ትንሳኤ ተዘርግቶ የሚያገኘውን መዝገብ እናቀርብለታለን"

ወደ ችሎቱ ቦታ ለመታደም የሚጓዙ ፍጡራን ጥብቅ ቁጥጥር
ይደረግባቸዋል

ﻭَﺟَﺎﺀﺕْ ﻛُﻞُّ ﻧَﻔْﺲٍ ﻣَّﻌَﻬَﺎ ﺳَﺎﺋِﻖٌ ﻭَﺷَﻬِﻴﺪٌ

"እያንዳንዷ ነፍስ ፣ አንደኛዋ ነጂና ሌላኛዋ መስካሪ በሆኑ ሁለት መልአክት ታጅባ ትመጣለች"

አድሎ የማይታሰብ ነው

"ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧَﺎ ﺑِﻈَﻠَّﺎﻡٍ ﻟِّﻠْﻌَﺒِﻴﺪِ "

" እኔም ለባሮቼ ፈፅሞ በዳይ አይደለሁም "

ተከላካይ ጠበቃ የለህም

ﺍﻗْﺮَﺃْ ﻛِﺘَﺎﺑَﻚَ ﻛَﻔَﻰٰ ﺑِﻨَﻔْﺴِﻚَ ﺍﻟْﻴَﻮْﻡَ ﻋَﻠَﻴْﻚَ ﺣَﺴِﻴﺒًﺎ

"የስራ መዝገብህን አንብብ። ዛሬ ራስህን ለመመርመር አንተው
በቂ ነህ።" (ይባላልም)።

ጉቦ ፣ አስታራቂ ዘመድ እና ባለስልጣን ከቦታው ዘር ይላሉ ማለት ፈፅሞ አይታሰብም።

ﻳَﻮْﻡَ ﻻ ﻳَﻨﻔَﻊُ ﻣَﺎﻝٌ ﻭَﻻ ﺑَﻨُﻮﻥَ

" ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን"

የስሞች መመሳሰል አይከሰትም

ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﺭَﺑُّﻚَ ﻧَﺴِﻴًّﺎ

"ጌታህ የሚረሳም አይደደለም።"

ፍርድን በእጅ መቀበል

ﻓَﺄَﻣَّﺎ ﻣَﻦْ ﺃُﻭﺗِﻲَ ﻛِﺘَﺎﺑَﻪُ ﺑِﻴَﻤِﻴﻨِﻪِ ﻓَﻴَﻘُﻮﻝُ ﻫَﺎﺅُﻡُ ﺍﻗْﺮَﺅُﻭﺍ ﻛِﺘَﺎﺑِﻴﻪ
ْ
" የስራ መዝገቡን በቀኝ እጁ የተቀበለ ሰው እንዲህ ይላል ያዙ፣ የስራ መዝገቤን አንብቡልኝ "

በአካል በሌሉበት ፍርድ የለም። ከችሎቱ አደባባይ
የሚያመልጥም ሆነ የሚቀር የለም።

ﻭَﺇِﻥْ ﻛُﻞٌّ ﻟَﻤَّﺎ ﺟَﻤِﻴﻊٌ ﻟَﺪَﻳْﻨَﺎ ﻣُﺤْﻀَﺮُﻭﻥَ "

" ሁሉም ከእኛ ዘንድ ለፍርድ ይሰበባሉ"

ፍርዱ አይሻርም፤ይግባይኝም የለው

ﻣَﺎ ﻳُﺒَﺪَّﻝُ ﺍﻟْﻘَﻮْﻝُ ﻟَﺪَﻱَّ

" ከኔ ዘንድ ቃሉ (የተላለፈው ፍርድ) አይለወጥም።"

ፍፁም የሆነ ፍትህ ሰፍኗል። የእዝነትና የምህረት ወቅት
አክትሟል። ብይኑ ተላልፏል። ከእንግዲህ የሚለወጥ ነገር የለም ነው መልዕክቱ።

በሀሰት የሚመሰክሩ ህሊና ቢስ ሰዎች በጭራሽ የሉም

ﻳَﻮْﻡَ ﺗَﺸْﻬَﺪُ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﺃَﻟْﺴِﻨَﺘُﻬُﻢْ ﻭَﺃَﻳْﺪِﻳﻬِﻢْ ﻭَﺃَﺭْﺟُﻠُﻬُﻢ ﺑِﻤَﺎ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻳَﻌْﻤَﻠُﻮﻥَ

" ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሠሩት በነበረው ሥራ ( እኩይ) በሚመሰክሩባቸው ቀን ( ከባድ ቅጣት አላቸው) "

የተረሱ ፋይሎች ፈፅሞ አይኖሩም

" ﻳَﻮْﻡَ ﻳَﺒْﻌَﺜُﻬُﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻓَﻴُﻨَﺒِّﺌُﻬُﻢْ ﺑِﻤَﺎ ﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ۚ ﺃَﺣْﺼَﺎﻩُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻧَﺴُﻮﻩُ ۚ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻰٰ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﺷﻬﻴﺪ "

" አላህ ሁሉንም ዳግም በሚቀሰቅሳቸውና እርሱ መዝገብ ውስጥ ያሰፈረውን እነርሱ ግን የዘነጉትን ተግባራቸውን
በሚነግራቸው ቀን። አላህ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነው።"

ፍፁም ትክክል የሆነ የስራ ሚዛን ይቀርባል

ﻭَﻧَﻀَﻊُ ﺍﻟْﻤَﻮَﺍﺯِﻳﻦَ ﺍﻟْﻘِﺴْﻂَ ﻟِﻴَﻮْﻡِ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ ﻓَﻠَﺎ ﺗُﻈْﻠَﻢُ ﻧَﻔْﺲٌ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﻭَﺇِﻥ ﻛَﺎﻥَ ﻣِﺜْﻘَﺎﻝَ ﺣَﺒَّﺔٍ ﻣِّﻦْ ﺧَﺮْﺩَﻝٍ ﺃَﺗَﻴْﻨَﺎ ﺑِﻬَﺎ ﻭَﻛَﻔَﻰٰ ﺑِﻨَﺎ ﺣَﺎﺳﺒﻴﻦ

" በትንሳኤ ቀን ፍትሃዊ ሚዛናችንን እናቆማለን። በመሆኑም ነፍስ ሁሉ ቅንጣት በደል አይደርስባትም። የሰነፋጭ ቅንጣት የምታክል ሥራ እንኳ ሳትቀር ለሚዛን እናቀርባታለን። ተቆጣጣሪነት በኛ በቃ "

መቆም ከማይቀርልን የችሎት አደባባይ ላይ ከመቆማችን በፊት
የስራ መዝገባችንን ለማሳመር እንትጋ። ጌታየ እዝነትህን እንሻለን ። የተኮረጀ ከከፊል Edition ጋ

@Tewihd