Get Mystery Box with random crypto!

#የላሟ እና የአላህ ፈሪው ልጅ ታሪክ ነብዩላህ ሙሳ አለሂ ሰላም ለበኒ እስራኤል ተልከው | አስ–ሱናህ

#የላሟ እና የአላህ ፈሪው ልጅ ታሪክ

ነብዩላህ ሙሳ አለሂ ሰላም ለበኒ እስራኤል ተልከው ኦሪትን ከመቀበላቸው በፊት አንድ አላህን የሚፈራ እና እናቱን የሚካድም ልጅ ነበር ።የሚተዳደርበት ሀብትና ንብረት ስላልነበረው በየቀኑ ሶስት ዲናር እንጨት እየሸጠ ነበር እናቱን የሚካድመው። ከሚያገኛት ሶስት ዲናር 1/3 ኛውን ለአቅመ ደካማ ምንም መስራት ለማይችሉ በቀን አንድ አንድ ዲናር፣ በወር 30 ዲናር ሰደቃ ይሰጥ ነበር።

እዚህ ጋር አንድ ነገር እንይ ይህ ወጣት ከሚያገኛት አነስተኛ ገቢ 1/3 ኛውን ሰደቃ መስጠት መቻሉን ስናይ እኛስ በቀን አንድ ብር ቀርቶ በወር ፣በሳምንት እንኳን ለእናቴ ለአባቴ ሶደቃ ብለን የማንሰጥ እንዲሁም የቤተሰብ ችግረኛን እንኳን ዙረን የማናይ ሆነን በአጠቃላይ ለዱንያ ፍቅር ምን ያህል ቦታ የሰጠን መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። እዚህ ጋር ሀቂቃ ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ ። ወደ ነበርንበት ታሪክ ስንመለስ

ወጣቱ ለሊቱን ቢሆን እንደ ቀን ውሎውን ለ3 በመክፈል 1/3 ኛው አላህን የሚገዛበት ሲሆን ቀሪው እናቱን የሚካድምበትና የሚያርፍበት ሰአት ነበር። በዚህ ላይ ሳለ የሚሸጠው እንጨት ተወዶ ሶስት ዲናር ይሸጥ የነበረውን ስድስት ዲናር ሽጦ ወደ እናቱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ለእናቱ ያማክር ስለነበር እስከዛሬ ሶስት ዲናር እሸጠው የነበረውን እንጨት የሚገዙኝ ሰዎች እጥፍ አድርገው በስድስት ዲናር ስለገዙኝ ሶስቱን ዲናር ምን ላድርገው ብሎ እናቱን ያማክራታል ።

እናቱ አላህን የምትፈራ ብልህና አዋቂ ስለነበረች "እንደዚህ ከሆነ ያንተ ስራ ከእጅ ወደ አፍ ነው ታመህ እንኳን ብትተኛ ምንም የምንሸጠው የምንለውጠው ነገር የለም ። ጊደር ግዛበት ምን አልባት አላህ ካለ ጊደሯ ብትወልድልን ወተት እና ቂቤ ልናገኝ እንችላለን ።ከቸገረንም እንሸጣታለን» ብለው እናት ልጃቸውን ይመክራሉ ።ልጅም የእናቱን ምክር በመቀበል በሶስት ዲናር አንዲት ጊደር ገዝቶ ይመጣል።

ከዛም ጊደሯን ሲጠብቅ ከዋለ ለእናቱም ሆነ ለራሱ ለሚስኪንም የሚሰጠው ሰደቃ እንደሚቋረጥ በተረዳ ጊዜ ይሄኔ ጊደሯን ሰው ወደሌለበት ጫካ ወስዶ ድምፁን ከፍ አድርጎ «ያአላህ» እያለ ለሶስት ጊዜ ተጣራ ከዚያም «ይህቺን ጊደር የሚጠብቅልኝ አጣው ለሰው ብሰጣት እንዳንተ የማምነው የለም ይህቺን ጊደር ጠብቅልኝ በፈለኩ ጊዜ ትሰጠኛለህ ጉዳት እንዳይደርስባት እንደ ምትጠብቅልኝ አልጠራጠርም» ካለ ቡሃላ «ሰማኸኝ»? «አዎ ሰምቼሀለው» በማለት ለራሱ ለጥሪው ምላሽ ከሰጠ ቡሃላ ጊደሯን ጫካ ወስጥ ትቶ እንጨቱን ተሸክሞ ወደ ቋሚ ስራው ይመለሳል

ከጥቂት ዘመን ቡሃላ እናቱ በሞት ሲለዩት ሚስት አግብቶ በትዳር እየኖረም ቢሆን በዛው እንጨት በመሸጥ ነበር የሚተዳደረው በዚህ ላይ እያለ እንደሚሞትና ወደ አኼራ እንደሚሄድ ህልም አይቶ ስለነበር ልጅ ልትወልድለት ፅንስ ለፀነሰቸው ባለቤቱ እንዲህ በማለት ኑዛዜ ይነግራታል ።

« እኔ የተረገዘውን ልጄን ለማየት አልታደልኩም እና ልጁ ከተወለደና ካደገ አባቴ ምን የተወልኝ ነገር አለ ካለ በእንደዚህ ጫካ ውስጥ ሄዶ ረከአተይን ለአላህ ሰግዶ ይጣራ አላህን ከተጣራ ቡሃላ « አባቴ የሰጠህን አደራ ስጠኝ ፥ ይበለው። በአደራ መልክ ለአላህ የሰጠሁለት ጊደር አለች እና አላህ ይሰጠዋል ይላታል።

ሚስቱም ብትሆን እንደ ባለቤቷ በአላህ ላይ ጠንካራ ተወኩል ስለነበራት በሰማቸው ነገር ሳትጠራጠር እሺ በማለት ትቆያለች። ልጅም ቢሆን ተወልዶ የአባቱን ስራ በመቀጠል እንጨት እየሸጠ እናቱን በመካደም ላይ ሳለ አንድ ቀን ለእናቱ «አባቴን በህይወት ባላገኘውም ለማስታወሻ የሚሆን ምንም ጥሎልኝ የሄደው የለም?» ብሎ ይጠይቃታል። እስከዚህ ሰአት ደረስ ረስታው ስለነበር አባቱ የነገራት ኑዛዜ ትዝ አላት እና «የልጄ ማስታወሻ ይሆናል ብሎ አባትህ ተናዞ ነው የሞተው ሁለት ረከአ ሰላት ለአላህ ሰግደህ ስትጨርስ ያአለህ ብለህ 3 ጊዜ ከተጣራህ ቡሃላ አባቴ የሰጠህን አደራ ብለህ ጠይቀው» አለችው

ልጁም እናቱ እንደነገረችው ወደ ተባለው ተራራ ሄዶ ........

........ ይቀጥላል

https://t.me/tewihd/