Get Mystery Box with random crypto!

ዐቂዳህን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ እወቅ! በትክክለኛው አቋምህ ላይ ፅና! ኢማሙ አልላ ለካኢ | አስ–ሱናህ

ዐቂዳህን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ እወቅ! በትክክለኛው አቋምህ ላይ ፅና!

ኢማሙ አልላ ለካኢይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«በአንድ ሰው ላይ ግዴታው የሀይማኖቱን የእምነት ቁንጮ (ፅንሰ ሀሳብ) ማወቅ ነው፣ እንዲሁም አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገውን ተውሒድን እና ባህሪውን መገንዘብ፣ መልእክተኛውን በእርግጠኝነት እውነት ብሎ አምኖ መቀበል፣ ወደ መንገዷም መድረስ ነው። በርሷ ላይም በማስረጃዎቿ ማስረጃ ማድረግ ነው።

ከተባለ ነገር ሁሉ ታላቁና ግልፅ የሆነው ማስረጃ እውነተኛና ግልፅ የሆነው የአላህ መፅሃፍ (ቁርኣን) ነው!!፣ ከዚያ በመቀጠል የመልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፋና (ሱንና/ሐዲስ) እና ፈሪሀ አላህ የሆኑና የተመረጡ የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች ንግግር ነው። ከዚያም በመቀጠል ደጋግ ቀደምቶች የጋራ አቋም የያዙበት (ኢጅማዕ) ያደረጉበት ነገር ነው።

ከዚያም በርሷ በሁሏም ላይ መጣበቅና እስከ ቀጠሮው ቀን (ምንዳ ሚሰጥበት ቀን) ድረስ ቀጥ ብሎ በፅናት መቆም ነው።

ከዚያም ከአዳዲስ ፈጠራዎች (ቢድዐ) ሁሉ መራቅና እንዲሁም ጠማሞች የፈጠሩትን ፈጠራ (ቢድዐ) ከመስማት መራቅ ነው።

ይህች ኑዛዜ (አደራ) የተወረሰችና ተከታትላ የመጣች የተጠበቀችና ከቀደምቶች የተያዘች፣ የተጓዙባት የሆነች መንገድ፣ ታዋቂ የሆነችው አመላካች፣ ጥልቅ የሆነችና የተረዳችዋ ማስረጃ ሶሃቦችና ተከታዮቻቸው ከነሱም በኋላ እነሱን የተከተሉት ልዩ ልዩ ሰዎችና አጠቃላዩ ሙስሊሞች የሰሩበት ነው።

በአለማቱ ጌታ አላህ እና በመካከላቸው ማስረጃ እንደሆነም እምነት አድርገው ይዘውታል። ከዚያም ቅን የሆኑ መሪዎችንና የተከተላቸውን ፋናቸውን የተከተለ እንዲሁም ፈሪሀ አላህ በሆኑ ሰዎች መንገድ የተጓዘ ሰው፣ አላህ እንዲህ ካላቸው ሰዎች ይሆናል:-

إِنَّ اللَّهَ مَعَ الَّذِينَ اتَّقَوا وَّالَّذِينَ هُم مُّحْسِنُونَ

«አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከሆኑት ጋር ነውና፡፡» አል ነህል 128

በዚህ መሰል ፍንተው ባለ መንገድ የያዘ ሰው፣ በዚህ ሸሪዓዊ መንገድ ማስረጃ የዘውተረ ሰው፣ በዚህች አለምና በቀጣዩም አለም የሚከተለው በሆነው ሀይማኖቱ ሰላም ይሆናል። መበጠስ የሌላት በሆነችዋም ገመድ (ዘለበት) ተጣብቋል። በአምሳያዋ የሚጠበቁባት በሆነችዋም ጋሻ ተጠብቋል። ኢንሻ አላህ በመጨረሻና በምንዳው ቀንም በረካዋም ይፋጠንለታል፣ መጨረሻዋም የተመሰገነ ይሆናል!!።

ከርሷ ቸል ብሎ ዘወር ያለ ሰው፣ ከርሷ ሌላ በሆነ ነገርም የሚያሰጠጋውን የፈለገ ሰው፣ ወደ ጥመት የሚወስደውን ነገር በመምረጡ ስቷል፣ ወደ ጥመት ገደልም ገብቷል። የጥመትን መንገድም ተጉዟል (መንገዱም ወደ አዘቅት) አውርዶታል። ከአላህ መፅሃፍ (ቁርኣን) እና ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፋና (ሀዲስ) ዘወር ያለ ሰው በጥፋት ዋሻ ውስጥ ነው። ቁርኣንና ሀዲስንም አላህ ማስረጃን ባላወረደበት በሆነው "አሉ ተባለ" ወሬ ተጋፍጧል። የተፍሲርና የቋንቋ ባለቤቶችም አያውቁትም! (እውቅናም አልሰጡትም)። የአዕምሮ ባለቤት በሆነ ሰው ልብ ላይም እንደ ማስረጃ አልወደቀም። የተውሒድ ሰዎች ልብም ለዚህ አስተሳሰብ አልተከፈተም!። በእርግጥም ሸይጧን ተጫውቶበታል!። ውርደትንም አከናንቦታል። አር-ረህማንን በማሳመፅም በቅጥፈትና በውሸት ራሱን እስኪሰቃቅል (እስከ ማክሯሯት) ደረጃ ድረስ አጥሞታል።» [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሉሱንና አልላ ለካኢይ 1/7]

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:–
«የአህሉሱንና ወልጀማዐ መንገድ ቀዳሚና አላህ አቡ ሀኒፋን፣ ኢማሙ ማሊክን፣ ኢማሙ ሻፊዒይን፣ ኢማሙ አሕመድን ከመፍጠሩ በፊት የሚታወቅ ነው። እሱም ከነቢያቸው የያዙት የሆነ የሶሃቦች መንገድ ነው። ይህን የተፃረረ ሰው አህሉሱና ወልጀማዐዎች ዘንድ ሙብተዲዕ ሆኗል።» ሚንሃጅ አስሱና 2/601

https://telegram.me/tewihd