2022-10-08 17:11:51
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ተፈተኛ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል
---------------------------------------------------
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ዝግጅት ምልከታ አካሂደዋል።
በዩኒቨርስቲው የተማሪዎች አቀባበል ሁኔታ ፣ የመፈተኛ ክፍሎች ዝግጅት እና በደህንነትን ለማስጠበቅ የተሰሩ ስራዎችንም ተመልክተዋል።
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ከማል አብዱረሂም (ዶ/ር) ዩኒቨርስቲው ትምህርት ሚኒስቴር በዘረጋው አሰራርና መመሪያ መሰረት ዩኒቨርስቲያቸው ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲው በግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ማስልጠኛ ኮሌጅና በፓዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተፈታኞችን እየተቀበለ ይገኛል።
በአሶሳ ዩኒቨርስቲ 10,021 ተማሪዎች በሁለቱም የትምህርት መስኮች የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን ይወስዳሉ።
ምንጭ:- የቤኒሻንጉል ክልል ትምህርት ቢሮ
475 views14:11