Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ temret_minster — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ temret_minster — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @temret_minster
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.79K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-07-01 16:33:37
የመውጫ ፈተና ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ የሚያርግ ስርዓት በመሆኑ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረዉ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ገለፁ፡፡
-------------------------------//------------------------
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ2015 ዓም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገዉ የመውጫ ፈተና መሰጠቱ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩና ተግተው እንዲማሩ የሚያርግ ስርዓት መሆኑን የሐሮማያ እና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ገልፀዋል፡፡
የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ልማትና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጀይላን ወልዬ ይህ ስርዓት መኖሩ ለትምህርት ጥራት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎች የበለጠ ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
ተማሪዎች በመጨረሻ ፈተና እንደሚወስዱ አውቀዉ ቀድሞው በአካል፣ በስነ-አእምሮና በስነ- ልቦና በመዘጋጀት ጠንክረዉ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የተለያዩ የስነ ልቦና ዝግጅትና የግንዘቤ ማስጨበጥ ስራዎችን እየተሰሩ እንዳሉ ገልፀዋል፡፡
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አብዱራህማን መክተል በበኩላቸዉ ይህ የመውጫ ፈተና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተማሪዎችን በስነልቦና ለማዘጋጀትና ከሂደቱም ጋር ከወዲሁ ለማለማመድ እንደ ዩኒቨርሲቲ ቀድመን ፕሮግራም በማዘጋጀት ሞዴል ፈተና ለመስጠት እየሰራን እንገኛለንም ብለዋል፡፡
1.4K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ