Get Mystery Box with random crypto!

, ለህይወቴ ትርጉም የሰጠችው እሷ ነች ብዬ አምን ነበር...በሷ ፍቅር ክንፍ ባልኩበት ወራት...የ | ጠባሴ ሚዲያ

, ለህይወቴ ትርጉም የሰጠችው እሷ ነች ብዬ አምን ነበር...በሷ ፍቅር ክንፍ ባልኩበት ወራት...የሰው ልጅ ለመኖር ምን ያስፈልገዋል ቢሉኝ...ምግብ፣ውሃ፣መጠለያ እና እሷ እል ነበር...ለእኔ ያን ያህል ታስፈልገኝ ስለነበር...

ሌት ተቀን ከእርሷ ሐሳብ ውጪ ሌላ ሐሳብ አልነበረኝም...የእኔን ሕይወት እርግፍ አድርጌ ትቼው የእርሷን ሕይወት ደባል ሆኜ የምኖርላት ይመስል ነበር...በእያንዳንዱ ነገሯ እጨነቃለሁ...

ታዲያ ይሄ ለእርሷ የገባት ጊዜ ችግር ሆነ...በእኔ ሕይወት ውስጥ ያላት ቦታ ሲገባት በእርሷ ሕይወት ውስጥ ቦታ ነፈገችኝ። እንደ አንድ ተራ እቃዋ እንኳን አልቆጥረኝ አለች...ነገር ተበላሸ።ሲሻት ከሕይወትህ ወጥቻለሁ ትላለች...እኔ እታወካለው...እናቶቻችን የሚያመልኩትን የሚለምኑትን አይነት ልመና እለምናታለሁ...የማንም ሁኚ ብቻ አትራቂኝ እላታለሁ። ከእኔ ለመራቅ የሞከረቻቸው እድሎች አልሳካ ሲሏት ትመለሳለች። በደስታ እቀበላታለሁ። ይህ ነገሯ ተደጋገመ! ስትሄድ ስለመናት፤ስትመጣ በደስታ ስቀበላት...ሰነበትን እና መንገድ የሆንኩ መሰለኝ...ወዴት እንደምወስድ ባላውቅም።


አንድ ቀን ልንዝናና ከተቀመጥንበት ቦታ እንዳለን...አጠገቤ በመኖሯ እንደንጉስ ተጀንኜ በኩራት በተቀመጥኩበት...እንደለመደችው ሳትመጣ "ልሄድ ነው" ብትለኝ...ኩስስ አልኩ።ተረጋግቼ ይሄ የመጨረሻዋ እንደሚሆን ለራሴ ማልኩለት።ከእንግዱህ በሬን ብታንኳኳ ላልከፍትላት ማልኩ...በእልህ ወደ ጆሮዋ ተጠግቼ እንዲህ አልኳት...


<መንገዱን ታውቂዋለሽ ወይስ ላሳይሽ?!>


ከተቀደደው ማስታወሻ
ናቲ