Get Mystery Box with random crypto!

'ጠልተኸኛል አይደል ?' አለቺኝ እንባ ባቀረሩ አይኖቿ አይኔን እያየች.... እንደ እውነቱ ከሆ | ጠባሴ ሚዲያ

"ጠልተኸኛል አይደል ?" አለቺኝ እንባ ባቀረሩ አይኖቿ አይኔን እያየች....

እንደ እውነቱ ከሆነ መልሱን አላውቀውም
ምን ልበላት?

አዎ ጠልቼሻለሁ !
እኔ ትልቅ ቦታ የምሰጣቸው ነገሮች ላንቺ ኢምንት ሆነው ስለምታጣጥያቸው ጠልቼሻለው!...ውድ ሐሳቦቼን ስለምታራክሽብኝ ጠልቼሻለሁ!...ለልፋቴ ምንም ዋጋ ሳትሰጪ እኔን ለመተቸት ትንሹን እንከኔን የተራራ ያህል ስለምታገዝፊ ጠልቼሻለው!...ከቸልተኝነት ይሆን ካለማወቅ ባልገባኝ መንገድ የእኔ ህይወት ላንቺ በጣም ቀላል መስሎ ስለሚታይሽ ጠልቼሻለሁ!
ልበላት?(ይሄም እውነት ነው።)


ቀና ብዬ ገረመምኳት የዘገየው መልሴ ይበልጥ ተስፋ አስቆረጣት...ተገድቦ የቆየው እንባዋ በጉንጮቿ ወረዱ...አሳዘነቺኝ...እንባዋ ውስጤ ይንቦገቦግ የነበረውን የንዴት እሳት አጥፍቶ አቀዘቀዘኝ...በጎ ነገሯ ታሰበኝ የዋህነቷ፣ለእኔ ያላት ፍቅር...ለድርድር እንደማታቀርበኝ...ለእኔ ብዙ እንደሆነች ታወሰኝ። (ይሄም እውነት ነው።)

ወደ ደረቴ አስጠግቼ አቀፍኳትና ስትጠብቀው የነበረውን ምላሽ ሰጠዋት...

አ ል ጠ ላ ሁ ሽ ም! (ከአንቺ ለመሻል ይሄን እውነት መረጥኩ።)


ከተቀደደው ማስታወሻ