Get Mystery Box with random crypto!

አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመ | ጠባሴ ሚዲያ

አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-

"የእርጅና ወራት ሳይመጣ በጉብዝና ወራት ፈጣሪህን አስብ!" የተባልከው እውነት ነው::
-
በፍቅር አምላክህን ካላሰብከው በህመም ታስበዋለህ::
-
ነፃ በሆንክ ሰዓት ያልጠራኸውን በእስር ስትወድቅ ተጠራለህ::
-
በጤና ያፈለከውን ስትታመም ትፈልጋለህ::በሰላም ያላዋራኸን አዳጋ ሲያጋጥምህ ታዋራለህ::
-
ሰዓቱ ደርሷል::አሁንም የመዳንህን እድል አታባክነው::በምድር ቅዠት ተኝተህ የአምላክህን መንግስት አትለፈው::
-
ምድር እንደሆነች ከጊዚያዊ እርካታ ውጪ የምትሰጥህ አንዳች የላትም::የሰጠችህንም ነገር አንድ በአንድ ቆጥራ ስትሞት ትቀበልሃለች::
-
ማንም ሰው ሊነጥቅህ የማይቻለውን መንፈስህን ብቻ ፈልገው::ነፃ የምትወጣው በእርሱ ነው::
-
አምላክህን ብትውደው ጊዜ እና ትኩረትህን በሰጠኸው ነበር::ድምፁን ለመስማት እና የአብሮነት ጊዜን ለማሳለፍ በተመኘህ ነበረ::
-
ነገሩ የማያውቁት አገር አይናፍቅም ሆኖል::በአለም አስትዳደግ አምላክህን እንድትረሳ ተደርጏል::ጠረኑ: ደግንቱ: ውበቱ: እርዳታው እና ቸርነቱ ጠፍቶሃል::አለም አታልሎህ ውስዶሃል::
-
እርሱ ግን ይወድሃል እና መቼም አይተውህም::ብትጠላው አይጠላህም::ህጉን ብታፈርስም አያፈርስህም::
-
ጠባዩ ሙሉ ፍቅር ነውና እስከ መጨረሻው ያፈቅርሃል::በፍቅር ካልሰማኸው በህመም ቢሆን እንድትቀርበው ይስብሃል::
-
አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-
እስቲ ደስስስ ይበለው ስማው::ልብህን ወደ እርሱ መልስ::የቀድመ የአባት እና የልጅ ፍቅራችሁን አድስ::እስቲ አንተ በትራህ አምላክህን ደስስስስ አሰኘው::ልቡን አብራላት::የፍቅር: የይቅርታ እና የሰላም ሰው ሁንለት::
-