ደመና የፀሐይን ብርሃን እንደሚጋርድ ክፉ ሀሳብም የአምላክን ፍቅር ይጋርዳል:: - አምላክ ባንቺ አንቺ ውስጥ ሲሆን አንቺ ደግሞ በአምላክ ውስጥ ሁኚ:: - እንቺ እሱን እንደምትፈልጊው እርሱም አንቺን እንደሚፈልግ እወቂ::የጠፉ ልጆቹን የምታድን መሳርያው ሁኝለት:: - የአለም መከራ "የአምላክ ፍቅር ለምን ራቀን?"ሊያብልሽ ይችላል::የአምላክ ፍቅር ርቆ ሳይሆን በክፉ የሰው ልጆች ሀሳብ ተጋርዶ እንደሆነ እወቂ:: - አለም ከመፈጠሯ አስቀድሞ የነብረ የህይወት የተገነባበት መሰረት የአምላክ ፍቅር ነው::ከአለም በኃላም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ሀይል ነው:: - ይህንን የፍቅር ሀይል በግልሽም ሆነ በአለም ህይወት ካላየሽው በክፉ ሀሳብ ተጋርዶብሻል ማለት ነው::አምላክ ባንቺ አድሮ አንቺንና ልጆቹን እንዳያድን ክፉ ሀሳብ ጋሬጣ ሆኖብሻል:: - ለምሳሌ ባንቺ ውስጥ ምን አይነት ሀሳቦች አሉ? እርግጥ ነው የገጠመሽ መጥፎ ነገር አለ::እርግጥ ነው ሰው በድሎሻል::እውነት ነው መሆን አልነበረብትም የሚያስብል ክፉ ነገር ገጥሞሻል:: - በክፉ ገጠመኝ ምክንያት በውስጥሽ ያዘልሻቸው ክፉ ሀሳቦች መልካሙን የአምላክ መንፈስ እንደሚጋርዱ እወቂ:: ባለማወቅ የሰው ልጆች በልባችን የምናስባቸው የሀጥያት እና የክፋት ሀሳቦች የአምላክ ብርሃንን ጋርደውብን ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል:: - ፈጣሪሽ እረኛሽ ከሆነ የሚያሳጣሽም የለም::ከሰውም ሆነ ከአለም አዲስ ነገር መጠበቅ አቁሚ::የሁሉም ነገር ምንጭ ከሆነው እርኛስ አምላክ ጋር ግንኙኑት ፍጠሪ:: - ግንኙነቱ የሚጀምረው ሀሳብን በማፅዳት ነው::ይህም ይቅርታ ወይም ንስሃ ይባላል::ለዘመናት በልብሽ ሲንከባለል የመጣው መጥፎ ሀሳብ ሲወጣ መልካሙ የአምላክ መንፈስ መግባት ይጀምራል:: - ይህ ቀላል ሂደት አይደለም::እያንዳንዱ ክፉ ሀሳብ ለብዙ ዘመን ባንቺ ውስጥ ስለኖረ በቀላሉ አይለቅሽም::ግን ቀላል የሆነውን አምላክ በፍፁም እምነት እና ፅናት ብትጠይቂው ያደርግልሻል:: 260 views ☞net, 19:18