Get Mystery Box with random crypto!

'ከአንድ ሚሊዬን ብር እና ከአንድ ሙዝ የቱ ይሻልሻል?' ተብላ ጦጢት ብትጠየቅ ምርጫዋ አንዱ ሙዝ | ጠባሴ ሚዲያ

"ከአንድ ሚሊዬን ብር እና ከአንድ ሙዝ የቱ ይሻልሻል?" ተብላ ጦጢት ብትጠየቅ ምርጫዋ አንዱ ሙዝ ነው::
-
አንድ ሚሊዬን ብር ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አታውቅምና:
-
"አሁን ተቀጥሮ ደሞዝ ከማግኘት እና አሁን ደክሞ ወደፊት የሚያተርፍ ቢዝነስ ከመጀመር የቱ ይሻላል?" ተብሎ ቢጠየቅ የብዙ ሰው ምርጫ
መቀጠር ነው::

-
ሪስክ ወስዶ ቢዝነስ መጀመር ከመቀጠር የበለጠ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ብዙ ሰው አያውቅምና::
-
አለማወቅ የወድቀት ሁሉ መሰረት ነው::አእምሯችን እውቀት አልባ ከሆነ ህይወታችን ፍሬ አልባ ይሆናል::መንፈሳችን ጥበብ ከሌለው ልፋታችን ስኬት የሌለው ይህናል::
-
ህይወት በብዛት የምትሰራው በጥበብ እንጂ በጉልበት አይደለም::በተለይ ባለንበት ዘመን የስኬት መግቢያ በሩ እውቀት እና መረዳት ነው::
-
ስለህይወት ምን ያህል ታውቃላችሁ? ሰዎች እንዴት ይሰራሉ? ገንዘብ ራሱ ምንድን ነው? የትዳራችሁን ደስታ ለመጨመር ምን ማወቅ አለባችሁ? ለደስታ : ለሰላምና ለፍቅር ሚስጥሩ ምንድን ነው?
-
ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎችም ሆነ ለማንኛውም የምድርና የሰማይ ኑሮ አስፈላጊ እውቀት አለ::ይህንን እውቀት ከእጁ ያስገባ የህይወት ሚስጥር ከእጁ ያስገባ ነው::
-
የራስ እውቀት ላይ የሚደረግ ኢንቬስትመንት አዋጭ ነው::ትርፉም ያረካል::እውቀት መቼም ሊጠፋ የማይችል ሀብት ነው::እውነተኛ እውቀት ያለው እውነተኛ ሀብታም ነው::
-
በጉልበት ከመኖር በእውቅት ወደ መኖር ተሸጋገሩ::
የምትፈልጉትን ነገር ወደ እናንተ የሚያመጣውን እውቀት ተማሩ::ዝም ብላችሁ ያገኛችሁትን "እውቀት!" ወደ ውስጥ አታስገቡ::እውቀታችሁ ከአላማችሁ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ይሁን::የወደዳችሁትን ነገር ወደ እናንተ የማያመጣ እውቀት ይቅርባችሁ::እያወራችሁ ብቻ የምትጎርሩብት እውቀት አለማወቅ ነው::
-
ማወቅ እውቀቱን ተግብሮ ውጤት ማምጣት ነው::