Get Mystery Box with random crypto!

1 ነት ጀምአ

የቴሌግራም ቻናል አርማ stopsadatkmal — 1 ነት ጀምአ 1
የቴሌግራም ቻናል አርማ stopsadatkmal — 1 ነት ጀምአ
የሰርጥ አድራሻ: @stopsadatkmal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 569
የሰርጥ መግለጫ

🍃 ነብያቺን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦ "ከእናንተ መካከል አንዳችሁ መጥፎ ነገርን ሲሰራ ካዬ ያንን ነገር በኃይል ተጠቅሞ ያስቁም ይሄን ማድረግ ካልቻለ በምላሱ ይቃወም ይህንንም ማድረግ ከተሳነው ያንን መጥፎ ነገር በልቡ ይጥላው በልቡ መጥላቱም ሁሉም በተሳነው ጊዜ ማድረጉ የሚወጅብበት የመጨረሻው ትንሹ ግዴታ ነዉ ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-29 03:37:44 ታላቁ አሊም ሸይክ አብዱሏህ አል ሀበሺይ እንዲህ ይላሉ
የሸሪአን ህግጋቶች መጠበቅ የሰውን ልጅን ሀሳብ ከመጠበቅ ይቀድማል።
218 viewsተቂዩዲን, 00:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 03:37:44
191 viewsተቂዩዲን, 00:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 00:51:42 ገና ሳይፈጠር ሰማይም ምድሩ
ሁሉም ሳይኖር በፊት ተራራም ሸንተሩ
እሱ ቀደመና ከፍጥረቱ ሁሉ
ለሱ ተብሎ ነው አለም መፈጠሩ
ለታቹም ለላዩም እሱ ነበር ሲሩ
የአደም መፈጠር ከአፈር ሰው መሆኑ
የሀዋ መገኘት ከአደም ከጎኑ
የሁሉም አንቢያእ በጊዜው ዘመኑ
የአደም መቶበት ሰበብ የመዳኑ
ያ ሁሉ ሰው ሰጥም ያመኑት ነጃት
በሰፊና ሰበብ በኑህ ዘመናት
የኢብራሂም መዳን ከፍሙ እሳት
ባህሩም መከፈሉ ለአስራ ሁለት
ለሙሳ ለሀሩን ደግሞም ላመኑት
የአዩብም መዳን መሆኑ አፊየት
ለሱ ብሎ ነው ለአለሙ እዝነት
ገና ሳይወለድ ከሆዷ ሳይወጡ
አጃኢባት ሁሉ ለአሚናት መጡ
መተው አበሰሯት ሁሉም ሙርሰሎች
አንቺ ያረገዝሽው ያለው በሆድሽ
የሁሉ አለቃ የትልቅ ትንሽ
ነብዩን ሙርሰል ነው የዲኑ አዳሽ
ከጌታው ጠይቆ ከሊሙሏህ ሙሳ
ኡመት ልሁን አለ ሙሀመድ ሲነሳ
አሏህ ተቀበለ የኢሳንም ጥሪ
ኡመቱ አድርገኝ ሱናውን ነሳሪ
አሏህም በአወል ኢሳንም መረጠው
የዘመን ማብቂያ ከሊፋ አደረገው
ዘሩን ምርጥ አረገው ጠበቀለት አሏህ
ከአደም ጀምሮ እስከ አባቱ አብዱሏህ
ሁሉም ንፁህ ሆኑ ክብሩ እንዲጎላ
አሏህም ከሁሉ ሲያልቀው ሲወደው
የሰው ልጅ መዳኛ እዝነት አርጎ ላከው
መጨረሻ መቶ ሁሉንም በለጠው
ኡመት በመሆኔ ፊቱንም ባላየው
በቁርአን ምመራ አሏህ ባወረደው
የነብዩን ሱና የበላይ በሆነው
ሙስሊም በመሆኔ ከሁሉ የላቀው
አልሀምዱሊላህ ምስጋና ይድረሰው
በእስልምና አድርገው መጨረሻዬን
አንተ በመረጥከው በወደድከው ዲን
አንተ በወደድከው በመረጥከው ዲን
221 viewsተቂዩዲን, 21:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 01:02:10 https://t.me/elmuahlisunamiftahuljenah
281 viewsተቂዩዲን, 22:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 01:01:49 https://t.me/elmuahlisunamiftahuljenah
238 viewsተቂዩዲን, 22:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 03:58:29 https://t.me/elmuahlisunamiftahuljenah
236 viewsተቂዩዲን, 00:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 23:38:38 የከሚስ ስጦታ
172 viewsተቂዩዲን, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 02:38:41 አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ባርያውን ወደ ገበያ ይልከዋል ባርያውም በጣም ከቆየ ቡሀላ እንዲገዛ ከተላከው ሁለት ነገር አንዱን ብቻ ገዝቶ ይመጣል አለቃውም በጣም ከገረፈው ቡሀላ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠው ከዚህ ቡሀላ አንድ ነገር ስልክህ ለሌላም ነገር እንደሚያስፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና ለምሳሌ ደብተር ብልክህ እስክሪብቶ እንደሚያሳፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና አለው።ባርያውም የአለቃውን ትእዛዝ ከተቀበለ ቡሀላ ወደስራው ተመለሰ።ከብዙ ጊዜ ቡሀላ አለቃው ይታመምና እኔ ሀኪም ቤት መሄድ ስለማልችል ሀኪም ይዘህ ና ብሎ ላከው።አገልጋዩም እንደለመደው በጣም ከቆየ ቡሀላ ሀኪሙንና ሌላ ተጨማሪ አንድሰው ይዞ መጣ።አለቃው ሀኪሙን ካየው ቡሀላ ሌላ ሰው ለምን አመጣህ ብሎ ጠየቀው አገልጋዩም ባለፍው ጊዜ ስትልከኝ አንድ ነገር ስልክህ ሁለተኛውም እንደሚያስፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና ብለሀኝ ነበር እኔም ሀኪሙ አክሞህ ከዳንክ ማሻ አሏህ ደስ ይላል ምናልባት ግን ህመምህ ጠንቶብህ ከሞትክ ይሄ ሰውዬ መቃብርህ ይቆፍራል አለው ይባላል።ፈገግታ ሱና ነው
211 viewsተቂዩዲን, 23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 02:29:15 አልሀምዱሊለሂ የሌለው ማቆሚያ
ቁርአንን ላረገው የኡማው መመሪያ
የነብዩ እድሜ አርባ እንደሞላ
ጅብሪል ይዞ መጣ ተልኮ ከመውላ
ዋሻ ውስጥ እንዳሉ የኛ ነብይ ውዱ
ጅብሪልም አላቸው ኢቅረእ ሙሀመዱ
መቅራትን አልችልም ካሉትም ቡሀላ
እሱም ተመላልሶ ደጋገመውና
በጀሊሉ ፍቃድ ልባቸው ላይ ፀና
ነቢም ተቀበሉ የዲን አደራ
ከልቁ ተቀብሎት በሱ እንዲመራ
የጌታ ችሎታው ጥበቡ እንዲቀራ
ጅብሪል አወረደው በኛ ከይረል ወራ
ተውራት ኢንጂል ነበር ከቁርአን በፊት
የሙሳ የኢሳ የነሱ ትምህረት
ቁርአንም መጣና ሁሉንም ቀደመው
በፊት ከነበሩት አሏህ አስበለጠው
የተከበረ ነው የሱ ንግግር
ዘላለም የሚኖር ነው የማይቀየር
ማንም አያመጣ ቁርአንን መሳይ
የሚኖር በምድር ቢሆን በሰማይ
በአለም አልታየም መቼም አይታይ
ግጥምም አደለ ወይ ስድ ንባብ
በሰው አልተፃፈም በቀለም በግንብ
የተወረደ ነው ከአለሙ ረብ
ምንኛ አማረ በሱ የተመራ
ከአሊም ተናንሶ ተምሮ ከቀራ
መንገድን አይስትም አይወድቅም አይጠፋ
አንተ ያሙጂቡ ቁርአን ያወረድከው
ቁረአንን የየልቤ ብርሀኔ አድርገው
የቀብሬን ጭርታ አስወጋጅ አድርገው
ነገም በቂያማ ምልጃዬ አድርገው
ዲኑንም ዱንያዬን በሱ አሳምረው
ነገም በቂያማ መስካሪዬ አድርገውው
172 viewsተቂዩዲን, 23:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ