Get Mystery Box with random crypto!

ገና ሳይፈጠር ሰማይም ምድሩ ሁሉም ሳይኖር በፊት ተራራም ሸንተሩ እሱ ቀደመና ከፍጥረቱ ሁሉ ለ | 1 ነት ጀምአ

ገና ሳይፈጠር ሰማይም ምድሩ
ሁሉም ሳይኖር በፊት ተራራም ሸንተሩ
እሱ ቀደመና ከፍጥረቱ ሁሉ
ለሱ ተብሎ ነው አለም መፈጠሩ
ለታቹም ለላዩም እሱ ነበር ሲሩ
የአደም መፈጠር ከአፈር ሰው መሆኑ
የሀዋ መገኘት ከአደም ከጎኑ
የሁሉም አንቢያእ በጊዜው ዘመኑ
የአደም መቶበት ሰበብ የመዳኑ
ያ ሁሉ ሰው ሰጥም ያመኑት ነጃት
በሰፊና ሰበብ በኑህ ዘመናት
የኢብራሂም መዳን ከፍሙ እሳት
ባህሩም መከፈሉ ለአስራ ሁለት
ለሙሳ ለሀሩን ደግሞም ላመኑት
የአዩብም መዳን መሆኑ አፊየት
ለሱ ብሎ ነው ለአለሙ እዝነት
ገና ሳይወለድ ከሆዷ ሳይወጡ
አጃኢባት ሁሉ ለአሚናት መጡ
መተው አበሰሯት ሁሉም ሙርሰሎች
አንቺ ያረገዝሽው ያለው በሆድሽ
የሁሉ አለቃ የትልቅ ትንሽ
ነብዩን ሙርሰል ነው የዲኑ አዳሽ
ከጌታው ጠይቆ ከሊሙሏህ ሙሳ
ኡመት ልሁን አለ ሙሀመድ ሲነሳ
አሏህ ተቀበለ የኢሳንም ጥሪ
ኡመቱ አድርገኝ ሱናውን ነሳሪ
አሏህም በአወል ኢሳንም መረጠው
የዘመን ማብቂያ ከሊፋ አደረገው
ዘሩን ምርጥ አረገው ጠበቀለት አሏህ
ከአደም ጀምሮ እስከ አባቱ አብዱሏህ
ሁሉም ንፁህ ሆኑ ክብሩ እንዲጎላ
አሏህም ከሁሉ ሲያልቀው ሲወደው
የሰው ልጅ መዳኛ እዝነት አርጎ ላከው
መጨረሻ መቶ ሁሉንም በለጠው
ኡመት በመሆኔ ፊቱንም ባላየው
በቁርአን ምመራ አሏህ ባወረደው
የነብዩን ሱና የበላይ በሆነው
ሙስሊም በመሆኔ ከሁሉ የላቀው
አልሀምዱሊላህ ምስጋና ይድረሰው
በእስልምና አድርገው መጨረሻዬን
አንተ በመረጥከው በወደድከው ዲን
አንተ በወደድከው በመረጥከው ዲን